መንግስት በኦሮምያ ያለው የኢንተርኔት አፈና እንዲያቆም ሂውማን ራይትስ ዎች ጠየቀ

(ERF)አለማቀፉ የሰብአዊ መብት ድርጅት ባወጣው መግለጫ በኦሮምያ ክልል ላለፉት 2 ወራት ኢንተርኔት እና ስልክ እንዲቋረጥ መደረጉ አግባብ አይደለም። አፈናው ነዋሪዎች እንደ ልብ እንዳይገናኙ፣ ህይወታቸውን በአግባቡ እንዳይመሩና ከመረጃ ውጭ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ስል ድርጅቱ ወቀሳ አቅርቧል።

በምዕራብ ኦሮምያ ቄለም ወለጋ፣ በምዕራብ ወለጋ  እና በሆድሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን እና በምስራቅ ወለጋ የስልክ መስመሮችና ኢንተርኔት ተቋርጧል። በአንዳንድ ዋና ዋና ከተሞች የጽሁፍ መልዕክት መለዋወጫ መንገዶች ብቻ ሲፈቀዱ ሌሎች ግንኙነቶች ተቋርጠዋል። እርምጃው የተወሰደው መንግስት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር አባላትን ለመቆጣጠር መሆኑን የጠቀሰው ሂውማን ራይትስ ወች፣ ይህንን ሰበብ በማድረግ መንግስት የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን መፈጸሙን የሚያሳይ ተጨባጭ መረጃ እንዳለው ጥቅሷል።

ድርጅቱ መንግስት የኢንተርኔት አፈናውን በአስቸኳይ እንዲያነሳም ጠይቋል።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: