የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ከግድያ አመለጡ

የሱዳንን የሽግግር መንግስት ለ 3 አመታት እንዲመሩ የተመረጡት ኢኮኖሚስቱ አብደላ ሃምዶክ ከግድያ  አምልጠዋል። ጠ/ሚኒስትሩ ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰባቸው አስታውቀዋል።

የጠ/ሚ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አሊ ባክሂት በጥቃቱ የተጎዳ ሰው አለመኖሩን ሲገልጹ የማስታወቂያ ሚኒስትሩ ደግሞ ድርጊቱን የሽብር ጥቃት ሲሉ ኮንነውታል።

ጥቃቱ ከቀድሞው ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር ባለስልጣናት ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል የማስታወቂያ ሚኒስትሩ ፍንጭ ሰጥተዋል።

የጄ/ል አለበሽር መንግስት  በህዝባዊና ወታድራዊ አመጽ ከተወገደ ወዲህ በሱዳን የተሳካ የመንግስት ሽግግር ለማምጣት የተደረገው የሽምግልና ጥረት ተሳክቶ ጠ ሚ/ር ሃምዶክ ከወታድራዊ አዛዦች ጋር አገሪቱን ለ 3 አመታት እንዲመሩ ተመርጠዋል። ጠንካራ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን የጀመሩት ጠ/ሚኒስትሩ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ተቃውሞ ሲቀርብባቸው ቆይቷል።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: