ዶ/ር አብይ አሕመድ በሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ላይ የተቃጣውን የግድያ ሙክራ አወገዙ

( ERF)ጠ/ሚኒስትር አብይ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ድርጊቱን አውግዘው፣ “እንዲህ ያሉ ክሥተቶች የሱዳንን መረጋጋትና የለውጥ ጉዞ ሊያደናቅፉ አይገባም።” ብለዋል።

ጠ/ሚኒስትር አብይ በሱዳን የተሳካ የሽግግር ስርዓት እንዲፈጠር እገዛ ማድረጋቸው ይታወቃል። የሱዳን መንግስት ከአባይ ጋር በተያያዘ ከኢትዮጵያና ግብጽ ጋር በሚደረገው ድርድር ከኢትዮጵያ ጎን በመቆሙ ከአረብ አገራትና ከግብጽ መንግስት ትችትን ሲያስተናግድ ሰንብቷል። የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ ለሱዳን መንግስት ያለውን አድናቆት ገልጿል።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: