ኢትዮጵያ የኮሮኖና ቫይረስ ካልገባባቸው ጥቂት አገራት መካከል አንዷ ሆነች

የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በፍጥነት እየተስፋፋ ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ ግን የበሽታው ምልክት እሰካሁን አልታየም። ይህም ኢትዮጵያን ቫይረሱ ካለገባባቸው ጥቂት አገራት ተርታ አሰልፏታል። የተለያዩ አለማቀፍ ስብሰባዎች እና የቱሪስት መዳረሻ በሆነችው ኢትዮጵያ ቫይረሱ እስካሁን አለመግባባቱ ብዙዎችን አስገርሟል።

ከአፍሪካ ግብጽ፣ አልጀሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሴኔጋል፣ ካሜሩን፣ ሞሮኮ ፣ ናይጀሪያ፣ ቱኒዚያ እና ቶጎ በሸታው ከተገኘባችወ አገራት ተርታ ተመድበዋል። በአሜሪካ ዩናይትድ ስቴስን ጭምሮ ብዙ አገሮች በበሽታው ተጠቅተዋል።

የበሽታው መነሻ አገር የሆነችው ቻይና በተጠቂዎች ቁጥር ቀዳሚውን ስፍራ ስትይዝ፣ ጣሊያንና ፣ ኢራን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ፈረንሳይና ጀርመንንም እንዲሁ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በሽታውን ለመከላከል እየወሰደ ያለውን እርምጃ አድንቀዋል። ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች ግን በሽታው ወደ ኢትዮጵያ አልገባም የሚለውን ለመቀበል ተቸግረዋል። በተለይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና የሚያደርገውን በረራ ባላቆመበት ሁኔታ፣ በሽታው ወደ ኢትዮጵያ አልገባም ብሎ መናገር እንደማይቻል አስተያየቶች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየቀረቡ ነው።

በሌላ በኩል ቻይና ለትምህርት የሄዱ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚያደርጉት ጥረት አለተሳካም። ኢትዮጵያውያኑ ወደ አገራቸው ለመመለስ ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርጉም የሚረዳቸው እንዳላገኙ በመገለጽ ኢትዮጵያውያን እንዲታደጉዋቸው መልዕክቶችን በማስተላለፍ ላይ ናቸው።  

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: