ከቱርክ የተላኩ ከፍተኛ የጦር መሳሪያዎች ተያዙ

(ERF) የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ 500 ሚሊዮን ብር ያክል ዋጋ ያላቸው እቃዎችና  የጦር መሳሪያዎች ከቱርክ ወደ ኢትዮጵያ በስውር መንገድ በጅቡቲ በኩል ሲገቡ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ከ18 ሺ በላይ ዘመናዊ ሽጉጦችና የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። የጦር መሳሪያው ቢሰራጭ ኖሮ ከፍተኛ ጉዳት ይደረስ እንደነበር መስሪያ ቤቱ ገልጿል።

ከጦር መሳሪያ ዝውውሩ ጋር በተያያዘ 24 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን መስሪያ ቤቱ ቢያስታውቅም፣ የሰዎችን ማንነት ግን ከመግለጽ ተቆጥቧል። በአገሪቱ የሚታየው የጦር መሳሪያ ዝውውር በተለያዩ አካባቢዎች ለሚታዩት ግጭቶች መባባስ ዋና ምክንያት ሆኗል።  

ቱርክ በኢትዮጵያ ለሚታየው የጦር መሳሪያ ዝውውር ዋና የግዢ ማዕከል ናት ።

https://ethio-redfox.com/

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: