የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወደ ተለያዩ የአረብ አገራት ተንቀሳቀሱ

(ERA) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሳምህ ሽኩሪ የአረብ አገራት በአረብ ሊግ ስብሰባ ላይ ላሳዩት ጠንካራ አቋም ለማመስገን እንዲሁም አገሮቹ በኢትዮጵያ ላይ ተጨማሪ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ለማግባባት የዲፕሎማሲ ዘመቻ ጀምረዋል።

ሚኒስትሩ ሳውዲ አረቢያን፣ ዩናይት አረብ ኢሚሬትስን፣ ኩዌትን፣ ባህሬንና ኦማንን ይጎበኛሉ። ሳውድ አረቢያና ዩናይት አረብ ኢምሬትስ በኢትዮጵያ ላይ ተጽዕኖ እንዲያሳድሩ የሚጠይቁት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ፣ ኢትዮጵያ በናይል ውሃ ላይ ብቸኛ ባለቤት ለመሆን የሚዳዳት፣ ዲፕሎማሲ የማይገባት አገር ናት ሲሉ ተናግረዋል።

ሱዳን የአረብ ሊግን መግለጫ ውድቅ በማድረጓ የግብጽ ሚዲያዎች ግብጽና የአረብ አገራቱ እርምጃ እንዲወሰዱ እየገፋፉ ነው።

ኢትዮጵያ ከግብጽ የሚሰነዘረውን ማስፈራሪያ ወደ ጎን ማለቷን ተከትሎ አንዳንድ የግብጽ ሚዲያዎች የኢትዮጵያን ወታደራዊ አቅም በተመለከተ ትንተና እያቀረቡ ነው። የአባይ ግድብ ስራ በተፋጠነ መንገድ መጓዙና በሚቀጥለው ሃምሌ ወር የውሃ ሙሌት ስራ ይጀመራል መባሉ፣ በ ፐሬዚዳንት አል ሲሲ ህዝባዊ ተቀባይነትና የፖለቲካ ህይወት ላይ ጥላ አጥልቷል። ፐሬዚዳንት ሲሲ አሁንም ተሰፋ ያደረጉት በአሜሪካ ላይ ነው። ይሁን እንጅ ወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የሚካሄድበት በመሆኑና ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከ አፍሪካ አሜሪካውያን  ተቃውሞ ሊደርስብኝ ይችላል በሚል ፍርሃት፣ ጉዳዩን በሃይል እየገፉብት እንዳልሆነም የግብጽ ሚዲያዎችን አሳስቧቸዋል።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: