ሼህ ሙሃመድ አልአሙዲ ለምን ወደ ኢትዮጵያ መመለስ አልቻሉም?

(ERF) ቢሊየነሩ ሼክ ሙሃመድ ሁሴን አልአመዱን በሙስና ወንጀል ተከሰው ከአንድ አመት በላይ ከታሰሩ በሁዋላ ባለፈው አመት ጥር ወር ላይ ቢፈቱም እስካሁን ሁለተኛ አገሬ ወደሚሏትና ከፍተኛ ሃብት ወደ አፈሩባት ኢትዮጵያ መመልስ አልቻሉም። ሚድሮክ ኢትዮጵያ በተባለው ድርጅታቸው ስር የሚገኙ አመራሮችና ሰራተኞች ሼኩ ከዛሬ ነገ ተመልሰው አመራር ይሰጣሉ ብለው ቢጠብቁም፣ ምኞታቸው ሊሰምር አልቻለም። በቅርብ ጊዜ ውስጥም ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ ተብሎ አይታሰብም። ሼክ አላሙዲ “ከትንሹ እስር ቢት ቢውጡም  ከትልቁ እስር ቤት ግን መውጣት አልተፈቀዳለቸውም” ይላሉ ጉዳዩን የሚያውቁ ሰዎች።

ሼክ አላሙዲን ከሙስና ጋር በተያያዘ እንደታሰሩ ይነገር እንጅ ፣ዋናው ጉዳይ ከአልጋወራሽ ሙሃመድ ቢን ሰልማን ስልጣን ጋር የተያያዘ ነው። የሳውድ አረቢያ ንጉሳውያን ቤተሰቦች ሙሃመድ ቢን ሰልማንን አባታቸውን በመተካት ቀጣዩ ንጉስ እንዳይሆኑ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ስጋት የገባው አልጋ ወራሹ፣ የቅርብ የስጋ ዘመዶችቻወን ሳይቀር በማሰር እንቅስቃሴውን ለማክሸፍ እየሞከረ ነው። አልጋወራሹ ተቃዋሚዎቼ ከሚላቸው ጋር  የቅርብ ወይም የሩቅ ግንኙነት ይኖራቸዋል ብሎ የሚገምታቸውን ባለሃብቶች ከአገር እንዳይወጡ ያገደ ሲሆን፣ ለአልጋ ወራሹ ያላቸውን ድጋፍ በተለያዩ መንገዶች እንዲገልጹም እያስገደደ ነው። ሼክ ሙሃመድ አላሙዲን አልጋወራሹን ለመበቀል ከተሰለፉ ሃይሎች ጎን ሊሰለፉ ይችላሉ በሚል ስጋት ከአገር እንዳይወጡ መደረጋቸውና በቁም እስር ላይ መሆናቸውን የቅርብ ሰዎች ይገልጻሉ።

 አልጋ ወራሹ በፍጥነት የአባታቸውን ቦታ ተክተው ስልጣኑን ካላደላደሉ በስተቀር ፣አላሙዲና መሰል ባለሃብቶች ከአገር የሚወጡበት እድል ላይኖር እንደሚችል ጉዳዩን በቅርብ የሚያወቁ ሰዎች ይናገራሉ።

ጠ/ሚ አብይ አህመድ ሼክ አላሙዲን ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካላቸውም።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: