ኢትዮጵያ የአሜሪካን ሽምግልና አልቀበልም ልትል ነው

የአሜሪካ መንግስት በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያን፣ ግብጽንና ሱዳንን ለማስማማት ያደረገውን ሙከራ አጥብቃ የኮነነችው ኢትዮጵያ ድርድሩ ከአሜሪካ እጅ ወጥቶ በአፍሪካውያን እጅ እንዲገባ ፍላጎት አላት ። ፐሬዚዳንት ትራምፕ በኢትዮጵያ ላይ ጫና በመፍጠር፣ ኢትዮጵያ አዲሱን እቅድ እንድትቀበለው እንደሚያደርጉ ለግብጹ መሪ ፕሬዚዳንት አል ሲሲ ገልጸው የነበረ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ ግን ከዚህ በሁዋላ የትራምፕን አስተዳደር ሽምግልና እንደማትቀበልና የአሜሪካ መንግስት በድርድሩ ለመሳተፍ ከፈለግ ግን እንደማትከለክለው ለማስታወቅ ተዘጋጅታለች።

ኢትዮጵያ ደቡብ አፍሪካ ድርድሩን እንድትመራ ሃሳብ አቅርባለች። ድርድሩም በአባይ ውሃ ላይ ሳይሆን በግድቡ ዙሪያ ብቻ እንዲሆን የኢትዮጵያ ፍላጎት ነው። እነዚህን አቋሞች የሚገልጽ ሰነድ በቅርቡ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል። የድቡብ አፍሪካው መሪ ራማፎዛ ሁለቱን አገራት ለመሸምገል ፍላጎት አሳይተዋል።

የአብይ አስተዳዳር በአባይ ውሃ ዙሪያ የያዘው አቋም ከፍተኛ ህዝባዊ ድጋፍ እያስገኘለት ነው። የኢትዮጵያ አቋም የአልሲሲን መንግስት አጣብቂኝ ውስጥ መጣሉንም የግብጽ ሚዲያዎች እየዘግቡ ነው።

ግብጽ ተስፋ የጣለችባቸውን የአረብ አገራት ለማሳመን ከፍተኛ የዲፕሎማቲክ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ብትሆንም፣ እስካሁን ይህ ነው የሚባል ተጨባጭ ውጤት አላገኘችም።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: