ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለግብጹ አቻቸው መልስ እየሰጡ ይሆን?

(ERF) ኢትዮጵያ በአሜሪካ ተዘጋጅቶ የቀረበውን የውሃ ስምምነት አልፈርምም ባለች ማግስት የግብጹ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ፣ ወታደራዊ አዛዦቻቸውን ሰብስበው ሲያናግሩ የሚያሳይ ፎቶ ለቀው ነበር። የፎቶው መልዕክት በቀጥታ ለኢትዮጵያ እንዲደርስ ተብሎ የተላከ ነው በሚል አስተያየት ሲሰጥበት ቆይቷል።

ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ደግሞ ለፎቶው ፖለቲካ የፎቶ ምላሽ ሰጥተዋል። በፌስቡክ ገጻቸውም እንዲህ ብለዋል፦

“ብሔራዊ የመከላከያ ሠራዊታችን አመራር እና አባላት ለሀገራቸው ያላቸው ፍቅር አስደናቂ ነው። ያላቸውን ሁሉ ለሀገራቸው ለመስጠት ፍጹም ቆራጦች ናቸው። ዛሬ ጠዋት ከአመራሮቹ ጋር የነበረኝ ስብሰባ በሠራዊታችን ያለኝን መተማመን የሚጨምር ነው፡፡”

ቀጣዩ ፉክክር ሚሳኤል እና ተዋጊ ጀቶችን ወደ ማሳየት ከፍ ሊል ይችላል።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: