ግድቡን ከቫይረስ ጥቃት ጠብቁት!

( ERF) የህዳሴው ግድብ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዳይጠናቀቅ የሚያደርግ አደጋ እየመጣ ነው። ግብጽም መተንፈሻ ልታገኝ ነው። ኮሮና ቫይረስ የሚባል አደገኛ በሽታ የግድቡን ስራ ሊያስተጓጉለውና በተያዘው የጊዜ ገደብ ውስጥ የውሃ ሙሌቱ እንዳይጀመር ሊያደርገው ይችላል። ለዚሁ ብዙ ክንያቶችን ማቅረብ ይቻላል። አንደኛ ለግድቡ ግንባታ የሚውሉ እቃዎች የሚገዙባቸው ብዙ አገሮች በበሽታው ተጠቅተዋል። እቃዎችን እንደልብ ገዝቶ ማስገባት አይቻልም። ቻይና፣ ፈረንሳይ፣... Continue Reading →

አንድ ኢትዮጵያዊ በኮሮና ቫይረስ ህይወቱ አለፈ

( ERF) ጣሊያን ውስጥ አንድ ኢትዮጵያዊ በኮሮና ቫይረስ ህይወቱ አለፎአል። የሟቹ ባለቤት በበሽታው የተያዘች ቢሆንም፣ የህክምና እርዳታ እየተደረገላት ይገኛል። የኢትዮጵያዊው ማንነት በውል አልታወቀም። ጣሊያን ውስጥ በቫይረሱ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ ነው። የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ፍጥነት መሰራጨቱ በመላው አለም ስጋትን ደቅኗል። በርካታ አገሮች ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ ሌሎች ህዝብ በብዛት የሚገኝባቸውን የስፖርትና የሙዚቃ ዝግጅቶችን እየሰረዙ... Continue Reading →

የህወሃት የምክር ቤት አባላት ፓርላማውን የተቃውሞ መግለጫ መድረክ ለምን አደረጉት?

"በህወሃት ዘመን አፋቸው የተለጎመ የፓርላማ አባላት በአብይ ዘመን አፋቸውን መፍታት ጀምረዋል" (ERF) በህወሃት የተሾሙ የምክር ቤት አባላት የተለያዩ መንግስታዊ ሹመቶችን ለማጽደቅ በሚሰበሰቡበት ወቅት፣ በአጀንዳው ላይ አስተያየታቸውን ከመስጠት ይልቅ፣ የብልጽግና ፓርቲን ህገ ወጥነት እና አገሪቱ ልትፈራርስ እንደቀረበች አድርጎ በማሳየት የፖለቲካ ስራ እየሰሩ ነው። የፓርላማ አባላቱ ክህወሃት በሚሰጣቸው አቅጣጫ መሰረት፣ ከአጀንዳ በውጣት ብልጽግና ፓርቲ ኢህዴግን ያፈረሰበት መንገድ... Continue Reading →

ኖርዌይ በርካታ ኢትዮጵያውያንን አሰረች

(ERF) ኖርዌይ ከአለፈው ሳምንት ወዲህ ከ 25 በላይ ኢትዮጵያውያንን አስራ ወደ አገራቸው ልትሸኝ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናትም የኖርዌይ መንግስት ኢትዮጵያውያኑን ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚያስችለውን ፈቃድ የሰጠ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ሰዎቹን ለማጓጓስ ተስማምቷል ። እርምጃው አለማቀፍ ህግን የሚጣረሰ ተደርጎ የሚታይ ነው ይላሉ ባለሙያዎች።በግዳጅ ከሚመለሱት መካከል ከ 14 አመታት በላይ የቆዩ ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል።

በመጪው ምርጫ ማን የተሻለ የማሸነፍ እድል አለው?

( ERF) በሚቀጥለው ነሃሴ ወር ላይ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው ምርጫ የተለያዩ አገራቀፍና ብሄር ተኮር ፓርቲዎች ይወዳደራሉ። የእነዚህ ፓርቲዎች እድሎችና ፈተናዎችን እንደሚከተለው እናቀርባለን። እናንተም ማን የተሻለ የማሽነፍ እድል እንዳለው አስተያየት ስጡበት ። ብልጽግና ፓርቲ ፓርቲው መንግስታዊ ተቋሙን የያዘ መሆኑ ፣ ከፍተኛ የገንዘብ አቅምና አደረጃጀትም ያለው በመሆኑ ከሌሎች ድርጅቶች በተሻለ የማሸነፍ እድል አለው። የፓርቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አብይ... Continue Reading →

የጠ/ሚ አብይ አህመድ አማካሪ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠማቸው

(ERF) የኢትዮጵያን ፕሬስ ድርጅት ለመምራት በቦርድ አባልነት የታጩት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በፓርላማ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል። ተቃውሞው በአብዛኛው ከሃይማኖት ጋር ተያይዞ የቀረበ ሲሆን፣ ከ 285 የፓርላማ አባላት ውስጥ 126ቱ የተቃውሞ ድምጻቸውን በመስጠት በቅርብ ጊዜ የፓርላማ ታሪክ ያልታዬ ተቃውሞ አጋጥሟቸዋል። ከጠ/ሚ አብይ ጋር መልካም የሚባል ግንኙነት እንዳላቸው የሚነገርላቸው ዲያቆን ዳንኤል፣ በአንዳንዶች ዘንድ እንደ አወዛጋቢ ሰው ይታያሉ። በቅርቡ... Continue Reading →

በኢትዮጵያ የሚገኙ የውጭ ድርጅቶች ስራ እያቆሙ ነው

( ERf) በኢትዮጵያ ውስጥ በአለማቀፍ ተቋማት ስር የሚገኙ ሰራተኞች የስራ እንቅስቃሴያቸውን በማቆም ላይ ናቸው። በተለያዩ አለማቀፍ ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች ቢሯቸውን እየዘጉ ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመመለስ ዝግጅት እያደረጉ ነው። ስራ የማቆሙ እርምጃ የተወሰደው ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ እንደሚሆን እየተነገረ ነው። በሽታው በኢትዮጵያ ውስጥ መግባቱ ባይነገረም፣ በውጭ ድርጅቶች ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ግን ከኢምባሲዎቻቸው በሚያገኙት ማስጠንቀቂያ መሰረት... Continue Reading →

ሳውድ አረቢያ በኢትዮጵያ ላይ የጉዞ ማዕቀብ ጣለች

( ERF) ሳውድ አረቢያ በኮሮና ቫይረስ ስጋት የተነሳ በኢትዮጵያ እና በሌሎችም አገራት ላይ የጉዞ ማዕቀብ ጥላለች ። ኢትዮጵያ እስካሁን አንድም የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ሰው መገኘቱን ባታስታወቅም፣ ከሳውድ አረቢያ የጉዞ ማዕቀብ ግን ማምለጥ አልቻለችም። እገዳው ለምን ያክል ጊዜ እንደሚቆይ አልታወቀም። ማዕቀቡን ተከትሎም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሳውደ አረቢያ የሚያደርገውን በረራ ሊያቋርጥ ይችላል። አየር መንገዱ ከኮሮና ቫይረስ... Continue Reading →

Blog at WordPress.com.

Up ↑