ሳውድ አረቢያ በኢትዮጵያ ላይ የጉዞ ማዕቀብ ጣለች

( ERF) ሳውድ አረቢያ በኮሮና ቫይረስ ስጋት የተነሳ በኢትዮጵያ እና በሌሎችም አገራት ላይ የጉዞ ማዕቀብ ጥላለች ። ኢትዮጵያ እስካሁን አንድም የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ሰው መገኘቱን ባታስታወቅም፣ ከሳውድ አረቢያ የጉዞ ማዕቀብ ግን ማምለጥ አልቻለችም። እገዳው ለምን ያክል ጊዜ እንደሚቆይ አልታወቀም። ማዕቀቡን ተከትሎም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሳውደ አረቢያ የሚያደርገውን በረራ ሊያቋርጥ ይችላል። አየር መንገዱ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የተጓዥ ቁጥር መቀነስ እንዳጋጠመው ገልጿል።

ሳውድ አረቢያ በጉዞ ማዕቀቧ ውስጥ ኤርትራን፣ ሱዳንን፣ ሶማሊያን፣ ጁቡቲንና የአውሮፓ ህብረት አገራትን አካትታለች ። በሳውድ አረቢያ በተለያዩ ስራዎች ተቀጥረው የሚገኙ ሰራተኞች አብዛኞቹ የውጭ አገር ዜጎች በመሆናቸው እገዳው የአገሪቱን ኢኮኖሚ በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዳዋል ተብሎ ይጥበቃል።

በሌላ በኩል አሜሪካ ለአንድ ወር የሚቆይ የጉዞ እቀባ ከእንግሊዝ በስተቀር ባሉና የሸንገንን ቪዛ በሚጠቀሙ  የአውሮፓ ህብረት አገራት ላይ የጉዞ ማዕቀብ ጥላለች። የአሜሪካ ውሳኔ የእቃዎችን ዝውውር እንደማይጨምር ፕሬዚዳንት ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: