በኢትዮጵያ የሚገኙ የውጭ ድርጅቶች ስራ እያቆሙ ነው

( ERf) በኢትዮጵያ ውስጥ በአለማቀፍ ተቋማት ስር የሚገኙ ሰራተኞች የስራ እንቅስቃሴያቸውን በማቆም ላይ ናቸው። በተለያዩ አለማቀፍ ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች ቢሯቸውን እየዘጉ ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመመለስ ዝግጅት እያደረጉ ነው። ስራ የማቆሙ እርምጃ የተወሰደው ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ እንደሚሆን እየተነገረ ነው። በሽታው በኢትዮጵያ ውስጥ መግባቱ ባይነገረም፣ በውጭ ድርጅቶች ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ግን ከኢምባሲዎቻቸው በሚያገኙት ማስጠንቀቂያ መሰረት ስራቸውን በማቆም ላይ ይገኛሉ።

ስራ በማቆም ላይ ያሉ አለማቀፍ ተቋማትን በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግስት እስካሁን የሰጠው መግለጫ የለም። በበሽታው የተነሳ ድሃ አገራት በከፍተኛ ሁኔታ ሊጎዱ ይችላሉ የሚል ፍርሃት አለ።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: