አንድ ኢትዮጵያዊ በኮሮና ቫይረስ ህይወቱ አለፈ

( ERF) ጣሊያን ውስጥ አንድ ኢትዮጵያዊ በኮሮና ቫይረስ ህይወቱ አለፎአል። የሟቹ ባለቤት በበሽታው የተያዘች ቢሆንም፣ የህክምና እርዳታ እየተደረገላት ይገኛል።

የኢትዮጵያዊው ማንነት በውል አልታወቀም። ጣሊያን ውስጥ በቫይረሱ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ ነው።

የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ፍጥነት መሰራጨቱ በመላው አለም ስጋትን ደቅኗል። በርካታ አገሮች ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ ሌሎች ህዝብ በብዛት የሚገኝባቸውን የስፖርትና የሙዚቃ ዝግጅቶችን እየሰረዙ ነው።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: