የህወሃት የምክር ቤት አባላት ፓርላማውን የተቃውሞ መግለጫ መድረክ ለምን አደረጉት?

“በህወሃት ዘመን አፋቸው የተለጎመ የፓርላማ አባላት በአብይ ዘመን አፋቸውን መፍታት ጀምረዋል”

(ERF) በህወሃት የተሾሙ የምክር ቤት አባላት የተለያዩ መንግስታዊ ሹመቶችን ለማጽደቅ በሚሰበሰቡበት ወቅት፣ በአጀንዳው ላይ አስተያየታቸውን ከመስጠት ይልቅ፣ የብልጽግና ፓርቲን ህገ ወጥነት እና አገሪቱ ልትፈራርስ እንደቀረበች አድርጎ በማሳየት የፖለቲካ ስራ እየሰሩ ነው።

የፓርላማ አባላቱ ክህወሃት በሚሰጣቸው አቅጣጫ መሰረት፣ ከአጀንዳ በውጣት ብልጽግና ፓርቲ ኢህዴግን ያፈረሰበት መንገድ ትክክል አይደለም በሚል ፓርቲውን ህገ ወጥ አድርገው ለማሳየት ተደጋጋሚ ሙከራዎችን  አድርገዋል። ብልጽግና ጸረ ትግራይ እንደሆነ እና በተለያዩ የሹመት ቦታዎች ላይ የትግራይ ተወላጆች እየተገፉ እንደሆነ በመናገር ፓርቲው በትግራይ ተቀባይነት እንዳይኖረው ይቀሰቅሳሉ።

የፓርላማ አባላቱ የፌደራል አቃቢ ህግ፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ፣ የገቢዎች ሚኒስትርና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባላትን ለመሾም በተሰየመበት ወቅት፣ የትግራይ የፓርላማ አባላት አጋጣሚውን ለጸረ ብልጽግና ቅስቀሳ ተጠቅመውበታል። ይህ ከጀንዳ ወጥቶ አስተያየት መስጠት ያልተለመደ አሰራር ቢሆንም፣ አፈጉባኤው ግን የፓርላማ አባላቱ እንዲናገሩ ፈቅደውላቸዋል።

በህወሃት ዘመን አንድም የፓርላማ አባል በመንግስት ላይ የተቃውሞ አስተያየት እንደማይቀርብ የሚያውቁት የፓርላማ አባላቱ፣ እንደ ልባቸው የሚናገሩበት መድረክ ማግኘታቸውን እንኳን ለማድነቅ አልደፈሩም። የትግራይ ክልል የፓርላማ አባላት ወደ ስብሰባ የሚመጡት፣ የተለመደውን አይነት አስተያየት ለመስጠትና ማንኛውንም በብልጽግና ፓርቲ የሚቀርበውን አጀንዳ ሁሉ ለመጣል መሆኑ፣ ሚዛናዊነታቸውን አዛብቶታል።

አሁን ባለው ሁኔታ አብዛኞቹ የብልጽግና ፓርቲ ደጋፊዎች የአማራ ክልል የፓርላማ አባላት ሲሆኑ፣ በኦሮምያ በኩል ለጠ/ሚኒስትሩ የሚሰጠው ድጋፍ በቅድመ ሁኔታ ላይ የተሰመረተ እየሆነ ነው። ድጋፉም ሆነ ተቃውሞው ብሄርን እንጅ ችሎታንና እውቀትን መሰረት ያደረገ እንዳለሆነ በገሃድ እየታየ ነው።

ጠ/ሚ አብይ አህመድ ቀጣዩ ፓርላማ ከብሄር ከዘር ወጥቶ በዋና ዋና አገራዊ አጀንዳዎች ላይ ትኩረት እንዲያደርግ በማሰብ፣ አሁን ያሉትን አብዛኞቹን የፓርላማ አባላት ከውድድር ውጭ እንደሚያደርጉዋቸው ይጠበቃል። ብዙዎቹም በድጋሜ እንደማይመረጡ በማወቃቸው አጋጣሚን ነጥብ  ማስቆጠሪያ እያደርጉት ነው። “በህወሃት ዘመን አፋቸው ተለጉሞ የነበሩ የፓርላማ አባላት አሁን በአይብ ዘመን አፋቸውን ፈቱ ሲሉ” አንድ የፓርላማ አባል ለሚዲያችን ተናግረዋል።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: