የጠ/ሚ አብይ አህመድ አማካሪ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠማቸው

(ERF) የኢትዮጵያን ፕሬስ ድርጅት ለመምራት በቦርድ አባልነት የታጩት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በፓርላማ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል። ተቃውሞው በአብዛኛው ከሃይማኖት ጋር ተያይዞ የቀረበ ሲሆን፣ ከ 285 የፓርላማ አባላት ውስጥ 126ቱ የተቃውሞ ድምጻቸውን በመስጠት በቅርብ ጊዜ የፓርላማ ታሪክ ያልታዬ ተቃውሞ አጋጥሟቸዋል።

ከጠ/ሚ አብይ ጋር መልካም የሚባል ግንኙነት እንዳላቸው የሚነገርላቸው ዲያቆን ዳንኤል፣ በአንዳንዶች ዘንድ እንደ አወዛጋቢ ሰው ይታያሉ። በቅርቡ በርካታ ሙስሊሞችና የኦሮሞ ብሄርተኞች ዲያቆን ዳንኤል ከአማካሪነት እንዲወርዱ ሲወተውቱ ሰንብተዋል።

ለድርጅቱ የቦርድ አባልነት ከተመረጡት መካከል አቶ አወል አብዲ፣ ኦባንግ ሜቶ፣ ማንያዘዋል እንደሻውና ወዳጄነህ መሃረነ ይገኙበታል።

ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከፍተኛ ተቃውሞ ቢቀርብባቸውም የቦርድ አባል ከመሆን አላገዳቸውም።

አቶ ዳንኤል በአንዳንድ የኦሮሞ ብሄርተኛ መሪዎች ላይ የሚሰነዝሩት የሰላ ትችት ከጠ/ሚኒስትሩ የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለማስፈጸም ነው በሚል ወቀሳ ይቀርብባቸዋል። በሚቀርብባቸው ወቀሳ ዙሪያ ብዙም መልስ የማይሰጡት አቶ ዳንኤል፣ በይፋ ያልታወቀ የማካሪነት ስልጣን እንዳላቸውና በብዙ ጉዳዮች ላይ ወሳኔ ሰጪ ሆነው እንዲሚቀርቡ ይገለጻል።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: