ግድቡን ከቫይረስ ጥቃት ጠብቁት!

( ERF) የህዳሴው ግድብ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዳይጠናቀቅ የሚያደርግ አደጋ እየመጣ ነው። ግብጽም መተንፈሻ ልታገኝ ነው። ኮሮና ቫይረስ የሚባል አደገኛ በሽታ የግድቡን ስራ ሊያስተጓጉለውና በተያዘው የጊዜ ገደብ ውስጥ የውሃ ሙሌቱ እንዳይጀመር ሊያደርገው ይችላል። ለዚሁ ብዙ ክንያቶችን ማቅረብ ይቻላል። አንደኛ ለግድቡ ግንባታ የሚውሉ እቃዎች የሚገዙባቸው ብዙ አገሮች በበሽታው ተጠቅተዋል። እቃዎችን እንደልብ ገዝቶ ማስገባት አይቻልም። ቻይና፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያንና ጀርመን ሰራተኞቻቸውን ቤት ማዋል ጀምረዋል። እቃ በፍጥነት ማዘዝና ማስገባት አይቻልም። ሁለተኛ በሽታው በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ የሚያደርሰው አደጋ ከፍተኛ ስለሚሆን፣ የአገሪቱ ገቢ በእጅጉ ይጎዳል። እቃዎችን እንደ ልብ መግዣ የውጭ ምንዛሬ ማቅረብ ሊከብድ ይችላል። የአለምም ኢኮኖሚ ስለሚጎዳ የኢትዮጵያ የወጭ ንግድም አብሮ ይጎዳል። ሶስተኛ ቫይረሱ ግድቡን በሚሰሩት ሰራተኞች ላይ ከታዬ ስራው በእጅጉ ይጎዳል።

ታዲያ መንግስት ምን ማድረግ አለበት? የመጀመሪያው እርምጃ በሽታው ወድ አገር ውስጥ እንዳይገባ፣ ከገባም እንዳይስፋፋ ፈጣን እርምጃ መውሰድ አለበት ። ወደ ጣሊያንና ቻይና የሚደረግ ጉዞ መቋረጥ አለበት ። የገቡ ቻይናውያን እንዳይወጡ፣ የውጡትም እንዳይገቡ መከልከል ወይም ለተወሰነ ጊዜ ለብቻ አግልሎ ማቆየት ። ወደ ግድቡ ለጉብኝት የሚሄዱ ሰዎች ሰራተኞችን እንዳይበክሉ ከአሁን በሁዋላ ጉብኝታቸውን እንዲያቆሙ ማድረግ። የግድቡ ሰራተኞችም ለተወሰነ ጊዜ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይንቀሳቀሱ ማገድ ይገባል።

እቃዎችን በተመለከተ የተወሰኑት በአገር ውስጥ ገበያ የሚገኙ ከሆነ በፍጥነት መግዛት እና ማስቀመጥ ። ለወደፊቱ የሚታዘዙ ከሆነ ግን ቁርጡ እስከሚለይ ማዘግየት ብቸኛ አማራጭ ነው። እቃዎች እንደተገዙ በሻማ ቢሆን እየተረዱ ስራውን ማቀላጠፍ ይገባል። እንዲህ ከሆነ የኮሮናን ጥቃት መቋቋም ይቻላል። ያም ሆኖ ግን ኮሮና በአባይ ግድብ ስራ አይ ፈተና ይዞ መምጣቱ አያጠያይቅም።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: