የኢትዮጵያ ነጋዴዎች ኮሮናን አስታከው ዋጋ ከመጨመር ይቆጠቡ!

( ERF) አንዳንድ ብሄራዊ አደጋዎች ሲከሰቱ ነጋዴዎች የዜግነት ግዴታ ተሰምቷቸው ምርቶቻቸውን ቢችሉ በቅናሽ ዋጋ ካለሆነም በገበያ ዋጋ መሸጥ ሲገባቸው፣ ከችግሩ ለማትረፍ የሚያደርጉት ሩጭ ብዙዎችን እያበሳጨ ነው ። በእርግጥም የኢትዮጵያ ነጋዴዎች ኢትዮጵያዊ ናቸው፤ ኢትዮጵያን የሚጎዳ ነገር ሲያጋጥም ከህዝቡ ጋር ሆነው ችግሩን መጋራትና ችግሩ እንዲቀረፍ መርዳት እንጅ በህዝቡ ጉዳት ለማትረፍ መሯሯጥ አይገባቸውም ነበር። ከሁሉም በላይ ደግሞ ሰዎች... Continue Reading →

አልጀዚራ በአባይ ጉዳይ ላይ ለምን ትኩረት ሰጠ?

(ERF) ታዋቂው አልጀዚራ ሚዲያ ከአባይ ግድብ ጋር በተያያዘ ተከታትይነት ያላቸውን ዘገባዎች እያቀረበ ይገኛል። በቅርቡ በግድቡ ዙሪያ ከሰራው ዘጋቢ ፊልም በተጨማሪ የኢትዮጵያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸውን ቃለ ምልልስ አድርጓል። ከሌሎች የአረብ ሚዲያዎች በተለዬ አልጀዚራ በኢትዮጵያ በኩል ያለውን ስሜት እያንጸባረቀ መሆኑ፣ ሚዲያው የአረብ አገራት ከያዙት አቋም የተለዬ ዘጋብ እንዴት ሊያቀርብ ቻለ የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም። በእርግጥም... Continue Reading →

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ተገኘ

( ERF) በኢትዮጵያ ውስጥ በአንድ የጃፓን ተወላጅ ላይ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ በሽታ መገኘቱን ከንቲባ የጤና ጥብቃ ሚኒስትር አረጋግጡ። ዶ/ር ሊያ ታደሰ እንዳሉት ጃፓናዊው ዜጋ ወደ አገር ውስጥ በገባ በ 5ኛው ቀን በሽታው እንዳለበት በኢትዮጵያውያን የላብራቶሪ ሰራተኞች ተረጋግጧል። ከግለሰቡ በቆይታው ሊያገኛቸው ይችላሉ የተባሉ 25 ሰዎች ክትትል እየተደረገባቸው ነው። ዶ/ር ሊያ ህብረሰተቡ እንዲረጋጋ ጠይቀዋል።

ዶ/ር አብይ አህመድ በፌስቡክ የድጋፍ ድምጽ የቀዳሚነቱን ስፍራ እንደያዙ ቀጥለዋል

( ERF) ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለረጅም ጊዜ በኦፌኮው አባል አቶ ጀዋር መሃመድ ተይዞ የነበረውን የኢትዮጵያን የፌስቡክ የድጋፍ ( ላይክ) ቁጥር መሪነት የተረከቡ ሲሆን፣ በተከታይ ብዛት (followers) ቁጥር ግን አሁንም አቶ ጀዋር እየመራ ነው። ይሁን እንጅ ዶ/ር አብይ የፌስቡክ ገጻቸውን በቅርቡ የጀመሩ በመሆናቸው በተከታይ ብዛት አንሰው ቢገኙም፣ የተከታዩ ቁጥር አሁን በሚታየው ፍጥነት የሚቀጥል ከሆነ በሚቀጥሉት ጥቂት  ወሮች... Continue Reading →

የኢትዮጵያ ወታደራዊ መኮንኖች የአባይ ግድብ ጉብኝት መልዕክቱ ምንድነው?

( ERF) የኢትዮጵያ አየር ሃይል ቁመና ምን ይመስላል? በኢትዮጵያ እና በግብጽ መካከል ያለው ፍጥጫ እየተካረረ በመሄድ ላይ ነው። ግብጽ ከዲፕሎማሲ ዘመቻ በተጨማሪ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር እየሞከረች ነው። የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ወደ ተለያዩ የአረብ አገራት እየዞሩ በኢትዮጵያ ላይ ተጨማሪ እርምጃዎች እንዲወሰዱ እየወተወቱ ነው። ኢትዮጵያም በቀድሞው ፕ/ት በዶ/ር ሙላቱ ተሾመና በፕ/ት ሳህለ... Continue Reading →

Blog at WordPress.com.

Up ↑