የኢትዮጵያ ወታደሮች ኦነግን አስጠግተዋል ያሉዋቸውን 5 ኬንያውያንን ገደሉ

 ( ERF) የኢትዮጵያ ወታደሮች የኦነግ አማጽያንን አስጠግተዋል ያሏቸውን 5 ኬንያውያንን ሴሲ በምትባል የድንበር ከተማ ላይ ገድለዋል።  ይህን ተከትሎም ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ የዋለ ሲሆን፣ በሞያሌም ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል። ወታደሮቹ  የሰዎችን ቤት ሰብረው በመግባት እርምጃ ወሰደዋል። የመንግስት ወታደሮች የኦነግ አማጽያንን ለመውጋት በተደጋጋሚ ወደ ኬንያ ድንበር እየገቡ እርምጃ ይወስዳሉ። በሁለቱ አገራት ድንበሮች አካባቢ ያለውን ውጥረት ለማርገብና ጸጥታውን... Continue Reading →

እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ከ25 ሺ ብር በላይ እዳ አለበት

( ERF) የገንዘብ ሚኒስቴር የቅርብ መረጃ እንደሚያሳየው፣ ኢትዮጵያ ከውጭና ከአገር ውስጥ ባንኮች የተበደረችው የገንዘብ መጠን 79 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። ከዚህ ውስጥ 53 ቢሊዮን 705 ሚሊዮን ዶላር ከውጭ አገራት የተገኘ ብድር ሲሆን፣ 27 ቢልዮን 29 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ከአገር ውስጥ ባንኮች የተገኘ ነው። ከውጭ እና ከአገር ውስጥ የተገኘው ብድር ለአጠቃላዩ የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር ሲካፈል እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ... Continue Reading →

ብልጽግና ፓርቲ ከ 1 ቢሊየን 500 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ሰበሰበ

“ የሚጠሉ  ከኮረና ቫይረስ ባልተናነሰ ውስጣቸውን ይበላሉ”  ዶ/ር አብይ አህመድ ፓርቲው ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ ባደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት 1 ቢሊዮን 500 ሚሊዮን ብር ሰብስቧል። የፓርቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አብይ አህመድ ሌሎች የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች እንዳሉ ገልጸዋል። በእነዚህ ዝግጅቶች የሚገኘውን ገቢ ለህዝብ ማስታወቅ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም እናካፍላለን  ብለዋል። ዶ/ር አብይ “ የሚጠሉ ሰዎች፣ የሚጠየፉ ሰዎች፣ የማይወዱ ሰዎች... Continue Reading →

በኮሮና ቫይረስ እስካሁን 2 ኢትዮጵያውያን ህይወታቸው አልፏል

( ERF) በጣሊያን ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ 2 ኢትዮጵያውያን ህይወታቸው ማለፉን ለማወቅ ችለናል።ኢትዮጵያውያኑ የህክምና እርዳታ ቢደረግላቸውም ህይወታቸው ሊተርፍ አልቻለም። ምን ያክል ኢትዮጵያውያን በበሽታው እንደተያዙ የሚያሳዩ መረጃዎችን ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም።

ኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ የደቀነው አደጋና የገንዘብ ተቋማቱ ምላሽ

(ERF) አይ ኤም ኤፍና የአለም ባንክ በኮርና ቫይረስ የተነሳ በአለም ላይ ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ቀውስ እንደሚፈጠር አስጠንቅቀዋል። በተለይ በድሃ አገሮች ቀውሱ የከፋ ይሆናል ይላሉ። ኢትዮጵያም ተጎጂ ከሚሆኑ አገራት መካከል አንዷ ናት። ይህንን ችግር ለመቋቋም እንዲያስችል አይ ኤም ኤፍ 50 ቢሊዮን ዶላር ፣ የአለም ባንክ ደግሞ 12 ቢሊዮን ዶላር መመደባቸውን አስታውቀዋል። የገንዘብ ተቋማቱ ለድሃ አገሮች የእዳ... Continue Reading →

ከቱርክ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡት የጦር መሳሪያዎች ለጀሃድ ወይስ ለንግድ?

( ERF) ካለፉት 3 ዓመታት ወዲህ ከቱርክ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። ባለፈው ሳምንት ብቻ 500 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ከ 13 ሺ በላይ ሽጉጦችና የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በጅቡቲ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ከገቡ በሁዋላ ተይዘዋል። 25 የኢትዮጵያ፣ የመንና ቱርክ ዜጎችም እጃቸው አለበት በሚል በቁጥጥር ስር ውለዋል። የጦር መሳሪያዎቹ ዋነኛ መነሻ... Continue Reading →

Blog at WordPress.com.

Up ↑