የኢትዮጵያ ወታደሮች ኦነግን አስጠግተዋል ያሉዋቸውን 5 ኬንያውያንን ገደሉ

 ( ERF) የኢትዮጵያ ወታደሮች የኦነግ አማጽያንን አስጠግተዋል ያሏቸውን 5 ኬንያውያንን ሴሲ በምትባል የድንበር ከተማ ላይ ገድለዋል።  ይህን ተከትሎም ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ የዋለ ሲሆን፣ በሞያሌም ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል።

ወታደሮቹ  የሰዎችን ቤት ሰብረው በመግባት እርምጃ ወሰደዋል።

የመንግስት ወታደሮች የኦነግ አማጽያንን ለመውጋት በተደጋጋሚ ወደ ኬንያ ድንበር እየገቡ እርምጃ ይወስዳሉ።

በሁለቱ አገራት ድንበሮች አካባቢ ያለውን ውጥረት ለማርገብና ጸጥታውን በቋሚነት ለማስከበር የሁለቱ አገራት መሪዎች በተደጋጋሚ ተገናኝተው ቢመክሩም ይህ ነው የሚባል መፍትሄ ሊገኝ አልቻለም።  

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: