በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር 4 ደረሰ

( ERF) ባለፈው ሳምንት አንድ ጃፓናዊ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘበት ከታወቀ በሁዋላ ከእርሱ ጋር ንክኪ የነበራቸው ሌሎች 3 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በጽሁፍ እንዳስታወቁት 117 ሰዎች  ከሌሎች ሰዎች ተለይተው ምርመራ እየተደረገላቸው ሲሆን እስካሁን 2 ጃፓናውያን እና አንድ ኢትዮጵያዊ በሽታው ተገኝቶባቸዋል። ሁሉም በጉልምስና እድሜ ውስጥ የሚገኙ ናቸው። የመጀመሪያው ህመምተኛ እያየገገመ እንደሆነም ዶከትሯ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ውስጥ አሁንም ህዝቡ በስፖርት፣ በሃይማኖት፣ በካፌዎችና በሌሎችም ዝግጅቶች በብዛት እየተገኘ ሲሆን፣ መንግስት እንደሌሎች አገሮች ብዛት ያላቸው ዜጎች የሚገኙባቸውን ዝግጅቶች አላገደም።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: