ኢትዮጵያ ገንዘብ ወደ ውጭ በማሸሽ በ3ኛ ደረጃ ላይ ተመደበች

( ERF) ገንዘብ ወደ ውጭ አገር ባመሽሸ ወይም በውጭ ባንኮች በህገወጥ መንገድ በማስቀመጥ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አገራት በ3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች ። ጥናቱን ያጠናው ታዋቂው የአሜሪካ የምርምር ተቋም ብሩኪንግስ ነው። ተቋሙ በዚህ ሳምንት ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያን ቀድመው የሚገኙ አገራት ደቡብ አፍሪካ እና ዲሞከራቲክ ሪፐብሊክ  ኮንጎ ናቸው። ከኢትዮጵያ ቀጥሎ ደግሞ ናይጀሪያ፣ ሪፕብሊክ ኮንጎና አንጎላ ከ 4 እስከ 6ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

ተቋሙ በጥናቱ በኢትዮጵያ እኤአ 1980 እስከ 2018 ባለው ጊዜ ውስጥ 84 ቢሊዮን 316 ሚሊየን ዶላር በህገወጥ መንገድ ወደ ውጭ ወጥቷል። ዋናዎቹ ተቀባይ አገሮች ደግሞ ቻይና፣አሜሪካ፣ ጃፓን፣ እንግሊዝ፣ ዩናይትድ አረብ ኢሚሬትስ፣ ጀርመን፣ ስፔንና ቤልጂየም ቀዳሚዎቹ እንደሆኑ ጥናቱ ያሳያል።  

አብዛኛው የኢትዮጵያ ገንዘብ ወደ ውጭ አገራት ባንኮች የገባው በህወሃት /ኢህአዴግ የአገዛዝ ዘመን ነው። ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ስልጣን እንደያዙ በተለያዩ አለማቀፍ ባንኮች በህገወጥ መንገድ ተከማችተው የሚገኙ ገንዘቦችን ለማስመለስ እንደሚሰሩ ተናግረው የነበረ ቢሆንም እስካሁን አልተሳካላቸውም። ብዙ ባለሃብቶችና ባለስልጣናት ገንዘቡን በስማቸው የማያስቀምጡ መሆኑ እንዲሁም ገንዘቡን ያስቀመጡባቸው ባንኮችና አገሮች ገንዘቡን ለመመለስ ትብብር ለማድረግ ብዙም ፈቃደኞች ስለማይሆኑ ገንዘብ ያማስመለሱን ሂደት አድካሚ ያደርገዋል።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: