ግብጾች ከኋይት ሃውስ ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ ሊያደርጉ ነው

 ግብጻውያን አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንድታደርግና የግብጽን የውሃ መብት እንድታስከብር ግፊት ለማድረግ በማሰብ በኋይት ሃውስ ፊት ለፊት እሁድ የተቃውሞ አለፍ ያደርጋሉ። አሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የተነሳ የህዝብን መሰባሰብ በከለከለችበት በዚህን ጊዜ፣ ሰልፉ በተያዘለት ሰዓት ይካሄድ አይካሄድ የሚታወቅ ነገር የለም።

ግብጽ አሜሪካ ያቀረበችውን ስምምነት ብትቀበልም፣ ኢትዮጵያ ውድቅ በማድረጓ ድርድሩ ተቋርጧል።

በሌላ በኩል የአፍሪካ መሪዎች በአባይ ጉዳይ የሚደረገው ድርድር ወደ አፍሪካ ህብረት እንዲዞር ኢትዮጵያ ያቀረበችውን ጥሪ እየተቀበሉ ነው። የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ሃሳቡን ደግፈው አስችኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ሃሳብ አቅርበዋል። ኬንያም ሃሳቡን መደገፏ ታውቋል።  የኢትዮጵያ የልኡካን ቡድን አባላት የዲፕሎማሲ ስራዎችን ለመስራት ወደ ተለያዩ አገሮች ተንቀሳቅሰዋል።  

በሌላ በኩል ሱዳን ኢትዮጵያና ግብጽን ለመሸምገል እንዳቀደች አስታውቃለች ። የሱዳን ከፍተኛ ወታደራዊ ጀኔራል ሙሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ እንዳስታወቁት አገራቸው በየጊዜው እያየለ የመጣውን የአካባቢውን ውጥረት ለመቀነስ ሲባል ሁለቱን አገራት ለማሸማገል አቅደዋል።

ደጋሎ ሃሳቡን ያቀረቡት ለሁለት ቀናት ያክል ግብጽን ከጎበኙና ከፕ/ት አል ሲሲ ጋር ከተገናኙ በሁዋላ ነው። ኢትዮጵያ ድርድሩ በሶስቱ አገራት ብቻ እንዲከናወን ስታስታውቅ ቆይታለች ። ሱዳንም የዚህ ሃሳብ ደጋፊ መሆኗን የጄኔራሉ ንግግር ያሳያል።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: