በነጋዴዎች ላይ የመጀመሪያ እርምጃ ተወሰደ ፓርላማው ስብሰባውን ሰረዘ

( ERF) መንግስት የኮሮና ቫይረስ ግርግርን አስመልክቶ የተጋነነ ዋጋ አቅርበው ህዝቡን ጎድተዋል ያላቸውን 83 ነጋዴዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል። የተያዙት ነጋዴዎች ምርቶችን በመከዘን የዋጋ ንረት እንዲፈጠር ያደረጉ ናቸው ሲል መንግስት ገልጿል።

መንግስት በዚህ ፍጥነት እርምጃ መውሰዱ ተገቢ ቢሆንም፣ በተሳሳተ መረጃና በበቀል ስም ነጋዴዎች እንዳይጎዱ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበትም አስተያየት ሰጪዎች ይገልጻሉ።

በዛሬው እለት የነጭ ሽንኩርትና የሎሚ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጭምሯል።

በሌላ በኩል ፓርላማው ሊያካሄድ የነበረውን ስብሰባ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሰርዟል።

የሃይማኖት አባቶች ደግሞ ህዝቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ቢያስታወቁም፣ ህዝቡ በአብያተ ክርስቲያናትና በመስጊዶች ለተወሰኑ ጊዜያት መሰብሰቡን እንዲያቆም ለመከልከል አልወሰኑም።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: