ኢትዮጵያ ትምህርትን እና ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን አገደች

( ERF) የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎችን ቁጥር መጨመር ተከትሎ ኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶችን፣ ስፖርታዊ ጨዋታዎችን፣ ትላልቅ ስብሰባዎችንና የመሳሰሉትን እንቅስቃሴዎች ለ2 ሳምንት ያክል እንዳይካሄዱ በመወሰን በርካታ የአለም አገራትን ተቀላቅላለች ። የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ባሉበት ቦታ ሆነው ክትትል እንደሚደረግላቸው የገለጹት ጠ/ሚ አብይ አህመድ፣ የንጽህና መጠበቂያ ሳሙናዎች በብዛት እንደሚሰራጩ አስታውቀዋል።

በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 5 መድረሱንና 5ኛ ግለሰብ ከዱባይ የመጣ መሆኑን ጠ/ሚ ግልጸዋል።

በትራንስፖርት የተነሳ የሚፈጠረውን መጨነናነቅ የግል ባለሃብቶችና የመንግስት መኪኖች ድጋፍ እንዲያደርጉ፣ የሃይማኖት ተቋማትንም ምዕመናኑ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጠ/ሚኒስትሩ መክረዋል።

እርምጃው ቢዘገይም፣ መልካም ውሳኔ መሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል። ኬኛ ከኢትዮጵያ ቀደም ብላ ተመሳሳይ እርምጃ ወስዳለች ።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: