የሎሚና የነጭ ሽንኩርት ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ አሻቀበ

(ERF) ሎሚና ነጭ ሽንኩርት ኮሮና ቫይረስን መከላከላቸው በሳይንስ ሳይረጋገጥ፣ ለበሽታው ጥሩ ነው በሚል ያልተረጋገጠ ወሬ የተነሳ ዋጋቸው በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። ነጭ ሽንኩርት እስከ 250 ብር እየተሸጠ ሲሆን፣ የሎሚም ዋጋ አሻቅቧል።

በሳሙናና አንዳንድ ሽቀጦችም ላይ የዋጋ ጭማሪ እየታዬ መሆኑ ህዝቡን አሳዝኗል። ነጋዴዎች ህዝቡን ለመርዳት መረባረብ ሲገባቸው ገና ለገና ሽብር በመንዛት የዋጋ ጭማሪ ማድረጋቸው ተገቢ አይደለም በማለት ነዋሪዎች ተናግረዋል። ህዝቡ ባልተረጋገጡ ወሬዎች የተነሳ የነጋዴዎች ሲሳይ እንዳይሆን፣ ነግሮችን በሰከነ መንገድ እንዲመለከትም አስተያየት ሰጪዎች ገልጸዋል። ጠ/ሚ አብይ አህመድ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉና ምርታቸውን በሚከዝኑ ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቀዋል።

ኬንያ ተመሳሳይ እርምጃ በነጋዴዎች ላይ መውሰድ ጀምራለች ።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: