ብልጽግና ፓርቲ ህወሃትን ለመፋለም መዘጋጀቱን አስታወቀ

( ERF) ኢህአዴግ ያለ ቀደሞ አባሉ ህወሃት እራሱን ወደ ብልጽግና ፓርቲ ካዞረ በሁዋላ ከህወሃት ጋር በሰላማዊ መንገድ ለመፋለም ይረዳኛል ያለውን የማደራጀት ስራ ጀምሯል። በሚኒስትር አብርሃ በላይ ( ፒ ኤች ዲ) የሚመራው የትግራይ ብልጽግ ፓርቲ፣ የጽህፈት ቤት ሃላፊውን መሾሙን አስታውቋል። በመቀሌ ዩኒቨርስቲ የስነጽሁፍ መምህር የነበሩት አቶ ነብዩ ስሑል ሚካኤል የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ሆነው መመደባቸውን ፣ የህዝብ ግንንዑነት ሃላፊው አቶ አውሉ አብዲ ገልጸዋል።

አቶ ነብዩ ስሑል ለውጡን የትግራይ ህዝብም እንደምፈልገው ተናግረዋል። የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ወጣት ምሁራንን እየሰበሰበ መምጣቱ በእድሜ በገፉ አረጋውያንን ለሚመራው ህወሃት ትልቅ ስጋት ደቅኗል። ህወሃት እነዚህን ወጣት አመራሮች “ባንዳዎች” የሚል ስያሜ የሰጣቸው ሲሆን፣ በማንኛውም መንገድ ሊፋለማቸው መዘጋጀቱን አስታዉቆ ነበር። ይሁን እንጅ ወጣት አመራሮቹ በብልጽግና ፓርቲ በመደገፍ ህወሃትን ማህበራዊ መሰረቴ ነው በሚለው የትግራይ ክልል ላይ ለመፋለም መዘጋጀታቸውን እየገለጹ ነው።

የፓርቲው ሊ/መንበር ዶ/ር አብይ አህመድ የትግራይ ህዝብ ከህወሃት አፈና በሂደት ነጻ እንደሚወጣ በቅርቡ ለፓርቲው መካከለኛ አመራሮች ተናግረዋል።

የብልጽግና የህወሃት አመራሮች እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ተከትሎ የህወሃት ደጋፊዎች በፌስቡክ የስድብ ወርጅብኝ እያወረዱባቸው ይገኛሉ።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: