በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የህብረት አምልኮ እገዳ ተጣለ

(ERF) የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በሚል መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የህብረት አምልኮን የከለከለች የመጀመሪያዋ የሃይማኖት ተቋም ሆናለች ። ቤተክርስቲያኗ ጥንቃቄ ማድረግ ማለት አለማመን አይደለም ያለች ሲሆን፣ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ሲባል ለሚቀጥሉት 2 ሳምንታት የእሁድ አምልኮ፣ ኮንፈረንሶች፣ ስልጠናዎችና ስብስባዎች እንደማይኖሩ አስታውቃለች ። ምዕመናኑ በሙሉ ከመጋቢት 11 እስከ 13፣ 2012 ዓም በጾምና በጸሎት በወረርሽኙ ጉዳይ ላይ ወደ እግዚአብሄር... Continue Reading →

የአሜሪካ ኢምባሲ ኢትዮጵያውያን በውጭ ዜጎች ላይ ጥቃት እየፈጸሙ ነው አለ

( ERF) በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ ባወጣው ማስጠንቀቂያ ከኮራና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ በሚኖሩ የውጭ አገር ዜጎች ላይ ጥቃት እየተፈጸመ ነው ብሎአል። ኢትዮጵያውያን ኮርናን ከፈረንጅ ወይም ከቻይና ጋር እያያዙ ጸያፍ የሆኑና የውጭ አገር ሰዎችን የሚያንቋሽሹ ስድቦችን እየተሳደቡ መሆኑን የሚያሳዩ በርካታ ሪፖርቶች ደርሶኛል ያለው ኢምባሲው፣ ኮሮናን ይዛችሁብን መጣችሁን በሚል ፣ ብዙዎቹ የትራንስፖርት አገልግሎት ሳይቀር ተከልክለዋል ብሏል። በድንጋይ... Continue Reading →

ኢትዮጵያ የነዳጅ አምራች አገራትን ልትቀላቀል ነው

( ERF) ኢትዮጵያ ከብዙ አስር አመታት በሁዋላ የነዳጅ አምራችና ላኪ አገራትን ልትቀላቀል ተቃርባለች። የአባይ ገድብ በሰላም ተጠናቆ ስራ ሲጀምርና ነዳጅ የማውጣቱና የመላኩ ስራ በተሳካ ሁኔታ ሲካሄድ፣ አገርቱ ሰፊ የኢነርጂ ገበያ ይኖራታል። ( ERF) አጼ ሃይለስላሴ እና ዲፕሎማቶቻቸው እነ አቶ አክሊሉ ሃብተወልድ፣ ጆን ስፔንሰር፣ ብላታ ኤፍሬምና ሌሎቹም ኦጋዴንን ከእንግሊዝ እጅ ለማስጣል ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ስራ ሰርተዋል። የጣሊያንን... Continue Reading →

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች የዓመት እረፍት እንዲወስዱ ጠየቀ

በኮሮና ቫይረስ የተነሳ ከፍተኛ የመንገደኞች ችግር ያጋጣመው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ሰራተኞች የአመት እረፍት እንዲወስዱ ጠይቋል። እርምጃው አየር መንገዱ እየደረሰበትን ያለውን የገንዘብ ኪስራ ለመቋቋም እንደ አንድ አማራጭ የተወሰደ ነው። ታዋቂው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሌሎች የአፍሪካና የአለም አየር መንገዶች በተለየ ወደ ቻይና የሚያደርገውን ጉዞ አልሰረዘም። ይሁን እንጅ ወደ ቻይና የሚጓዙ መንገደኞች በመቀነሳቸው አየር መንገዱ ሌሎች አማራጮችን ለመውሰድ... Continue Reading →

የአገሪቱ መከላከያ ሰራዊት ከካምፕ እንዳይወጣ ታዘዘ

( ERF) የኮሮና ቫይረስን ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላልተወሰ ጊዜ ከካፕ እንዳይወጣ ታዟል። የአመት ፈቃድ ወይም የአንድ ቀን የከተማ ፈቃድም እንዲሁ ላልተወሰነ ጊዜ ተከልክሏል። የመከላከያ ሰራዊት ኤታማዦር ሹም ጄ/ል አደም መሃመድ እንደተናገሩት የቤተሰብ ጥየቃም ሆነ አዳዲስ የሰራዊት አባላትን መመልመል ከዛሬ ጀምሮ ተቋርጧል። እስካሁን ባለው መረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ የመከላከያ ሰራዊት አባል አለመኖሩንም ጀኔራሉ አክለው... Continue Reading →

Blog at WordPress.com.

Up ↑