በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የህብረት አምልኮ እገዳ ተጣለ

(ERF) የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በሚል መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የህብረት አምልኮን የከለከለች የመጀመሪያዋ የሃይማኖት ተቋም ሆናለች ።

ቤተክርስቲያኗ ጥንቃቄ ማድረግ ማለት አለማመን አይደለም ያለች ሲሆን፣ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ሲባል ለሚቀጥሉት 2 ሳምንታት የእሁድ አምልኮ፣ ኮንፈረንሶች፣ ስልጠናዎችና ስብስባዎች እንደማይኖሩ አስታውቃለች ።

ምዕመናኑ በሙሉ ከመጋቢት 11 እስከ 13፣ 2012 ዓም በጾምና በጸሎት በወረርሽኙ ጉዳይ ላይ ወደ እግዚአብሄር እንዲጸልዩም ቤተ ክርስቲያኗ ጠይቃለች ።

የሃይማኖት ተቋሟት ጉባኤ ሰሞኑን ህዝቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ምክር ቢለግስም፣ ህዝቡ በጋራ ከማምለክ እንዲቆጠብ አልከለከሉም። የአለም የእስልምና ማዕከል የሆነችው ሳውድ አረቢያ በመካና በመዲና ከሚገኙ ሁለት መስኪዶች በስተቀር ሁሉም መስጊዶች እንዲዘጉ አዛለች ። ቫቲካንም ዘወትር እሁድ የምታደርገውን የህዝብ ጉባኤ ሰርዛለች ።   

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: