የአሜሪካ ኢምባሲ ኢትዮጵያውያን በውጭ ዜጎች ላይ ጥቃት እየፈጸሙ ነው አለ

( ERF) በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ ባወጣው ማስጠንቀቂያ ከኮራና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ በሚኖሩ የውጭ አገር ዜጎች ላይ ጥቃት እየተፈጸመ ነው ብሎአል።

ኢትዮጵያውያን ኮርናን ከፈረንጅ ወይም ከቻይና ጋር እያያዙ ጸያፍ የሆኑና የውጭ አገር ሰዎችን የሚያንቋሽሹ ስድቦችን እየተሳደቡ መሆኑን የሚያሳዩ በርካታ ሪፖርቶች ደርሶኛል ያለው ኢምባሲው፣ ኮሮናን ይዛችሁብን መጣችሁን በሚል ፣ ብዙዎቹ የትራንስፖርት አገልግሎት ሳይቀር ተከልክለዋል ብሏል።

በድንጋይ የተመቱ ፣ ምራቅ የተተፋባቸው እንዲሁም ከድብደባ በሩጫ ያመለጡ የውጭ አገር ሰዎች መኖራቸውን በመጥቀስ። በአገሪቱ የሚኖሩ የውጭ አገር ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መክሯል።

የኢትዮጵያ መንግስት ፈጥኖ ምላሽ ካልሰጠ ወይም ድርጊቱ እውነት ከሆነ ጠንካራ እርምጃ በመውሰድ ጥቃቱን ካልተቆጣጠረ፣ የኢምባሲው ማስጠንቀቂያ የአገሪቱን ገጽታና የቱሪዝም ገበያ በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዳዋል።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: