የአገሪቱ መከላከያ ሰራዊት ከካምፕ እንዳይወጣ ታዘዘ

( ERF) የኮሮና ቫይረስን ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላልተወሰ ጊዜ ከካፕ እንዳይወጣ ታዟል። የአመት ፈቃድ ወይም የአንድ ቀን የከተማ ፈቃድም እንዲሁ ላልተወሰነ ጊዜ ተከልክሏል። የመከላከያ ሰራዊት ኤታማዦር ሹም ጄ/ል አደም መሃመድ እንደተናገሩት የቤተሰብ ጥየቃም ሆነ አዳዲስ የሰራዊት አባላትን መመልመል ከዛሬ ጀምሮ ተቋርጧል። እስካሁን ባለው መረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ የመከላከያ ሰራዊት አባል አለመኖሩንም ጀኔራሉ አክለው ተናግረዋል።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: