የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች የዓመት እረፍት እንዲወስዱ ጠየቀ

በኮሮና ቫይረስ የተነሳ ከፍተኛ የመንገደኞች ችግር ያጋጣመው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ሰራተኞች የአመት እረፍት እንዲወስዱ ጠይቋል። እርምጃው አየር መንገዱ እየደረሰበትን ያለውን የገንዘብ ኪስራ ለመቋቋም እንደ አንድ አማራጭ የተወሰደ ነው።

ታዋቂው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሌሎች የአፍሪካና የአለም አየር መንገዶች በተለየ ወደ ቻይና የሚያደርገውን ጉዞ አልሰረዘም። ይሁን እንጅ ወደ ቻይና የሚጓዙ መንገደኞች በመቀነሳቸው አየር መንገዱ ሌሎች አማራጮችን ለመውሰድ ተገዷል።

ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ የሆነ የውጭ እዳ አለበት።

በአጠቃላይ የአፍሪካ አየር መንገዶች ወደ ቻይና የሚያደርጉትን በረራ በመሰረዛቸው ብቻ ከ 400 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያጡ የአፍሪካ የአየር መንገድ ማህበር አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና የሚያደርገውን በረራ በሚመለከት የሚቀርብበትን ትችት ውድቅ ያደርገዋል። ድርጅቱ ከአለማቀፍ የጤና ድርጅት በሚሰጠው አቅጣጫና ምክር እየታገዘ የበረራ መስመሩን እንደሚቀይስ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ይናገሯሉ።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: