የፋኖና የአማራ ክልል መንግስት ፍጥጫ

ሪፓርታዥ ( ERF) በኢትዮጵያ የተፈጠረውን ለውጥ ተከትሎ የህወሃትን መንግስት በዱር በገደሉ ሲዋጉ የነበሩ ታጋዮች አንዳንዶች ትጥቃቸውን እያስረከቡ ሌሎች ደግሞ እስከነ ትጥቃቸው ሰላማዊውን የፖለቲካ ትግል ተቀላቀሉ። ኤርትራ የነበሩት እንደ ኦነግ፣ አርበኞች ግንቦት7 እና አዴሃን የመሳሰሉ “ነጻ አውጪዎች” ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ በድል አድራጊነት መንፈስ ከፍተኛ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ሌሎች በአገር ውስጥ ሆነው ሲደራጁ የነበሩት፣ በተለይ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ... Continue Reading →

በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሱቆች ከመዘጋታቸው በፊት በፍጥነት የጎደላቸውን እንዲያሟሉ አምባሳደሩ አሳሰቡ

( ERF) በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ፍጹም አረጋ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ እንደጻፉት በአሜሪካ የኮሮና ቫይረስ በፍጥነት እየተሰራጨ በመሆኑ፣ "ከዛሬ 5:00 pm ጀምሮ በመላው አሜሪካ ሁሉም ተቋማት የንግድ ተቋማትን ጨምሮ ለ2ሳምንት እንደሚዘጉና ሁሉም በየቤቱ ኳራንቲን በመሆን የኮሮና ቫይረስን ስርጭት ለመከላከል እንደታሰበ ስለሰማሁ በቀራችሁ 5 ሰዓት የጎደላችሁን በማሟላት ወደ ቤታችሁ እንድትሰባሰቡ ይህንን ጥቆማ በአክብሮት አደርሳለሁ:: ራቅ ያለ... Continue Reading →

ገዱ አንዳርጋቸው ትክክለኛው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናቸው ?

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት በነበሩበት ወቅት ተወዳጅ ነበሩ። ታጋሽ፣ አድማጭ፣ ነገሮችን ከሩቅ ማሽተት የሚችሉ፣ ተግባቢና በሳል ሰው እንደሆኑ በቅርብ የሚያውቋቸው ሰዎች ይናገራሉ። እርሳቸው ክልሉን ሲመሩ በነበረበት ወቅት ከህወሃት ይደርስባቸው የነበረውን ተደጋጋሚ ጫና ተቋቁመው፣ የህወሃት አገዛዝ እንዲወገድ ከፍተኛ ስራ ሰርተዋል። ከኦህዴድ ጋር ሚስጢራዊ ግንኙነት  በመመስረትም፣ ህወሃት አማራና ኦሮሞን ለማጋጨት እና ስልጣን ላይ ለመቆየት ያደረግ... Continue Reading →

ታላላቅ የአለም ሚዲያዎች ኢትዮጵያውያን በውጭ አገር ዜጎች ላይ የፈጸሙትን ጥቃት እየዘገቡት ነው

( ERF) ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በውጭ አገር ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ ካስታወቀ በሁዋላ ታላልቅ የሚባሉት የአለም የመገናኛ ብዙሃን ዜናውን እያራገቡ ነው። ቢቢሲን ጨምሮ ዘ ሂል እና ሌሎችም የመገናኛ ብዙሃን እያራገቡት ነው። ጥቃቱ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚሰሩ ጋዜጠኞችም ላይ ያነጣጠረ ነው። የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ " ቫይረሱ ከየትኛውም ሀገር ወይም ዜግነት... Continue Reading →

ቤተሰቦች ከእስረኞች ጋር እንዳይገናኙ እገዳ ተጣለ

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ሲባል በፌደራል ደረጃ የሚገኙ እስረኞች ለሁለት ሳምንታት ያክል ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዳይገናኙ እገዳ ተጥሏል። ፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር በአገሪቱ ከተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ታራሚዎችን ለመጠበቅ ሲባል ለመጪዎቹ 15 ቀናት ታራሚዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዳይገናኙ እግድ መጣሉን አስታውቋል። እስረኞቹ ወደ ሆስፒታል የሚሄዱት የከፋ ችግር ከገጠማቸው ብቻ መሆኑ ያስታወቀው የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር፣ እስካሁን ድረስ... Continue Reading →

Blog at WordPress.com.

Up ↑