በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሱቆች ከመዘጋታቸው በፊት በፍጥነት የጎደላቸውን እንዲያሟሉ አምባሳደሩ አሳሰቡ

( ERF) በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ፍጹም አረጋ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ እንደጻፉት በአሜሪካ የኮሮና ቫይረስ በፍጥነት እየተሰራጨ በመሆኑ፣ “ከዛሬ 5:00 pm ጀምሮ በመላው አሜሪካ ሁሉም ተቋማት የንግድ ተቋማትን ጨምሮ ለ2ሳምንት እንደሚዘጉና ሁሉም በየቤቱ ኳራንቲን በመሆን የኮሮና ቫይረስን ስርጭት ለመከላከል እንደታሰበ ስለሰማሁ በቀራችሁ 5 ሰዓት የጎደላችሁን በማሟላት ወደ ቤታችሁ እንድትሰባሰቡ ይህንን ጥቆማ በአክብሮት አደርሳለሁ:: ራቅ ያለ መንገድ የጀመራችሁም ብትመለሱ ጥሩ ነው::” የሚል ምክር ለግሰዋል።

“ይህንንም ለማስፈጸም በመላው አሜሪካ ወታደር ሊሰማራ መሆኑንም ሰምቻለሁ” ሲሉ የገለጹት አምባሳደሩ፣ ” መጠንቀቅ እንጂ መደናገጥ ተገቢ እይደለም::” ሲሉ አክለዋል።

ፕ/ት ትራምፕ ራሳቸውን የጦርነት ጊዜ ፕሬዚዳንት አድርገው የሾሙ ሲሆን በሽታውን ለመከላከል ይበጃል የሚሉትን እርምጃ ሁሉ እንደሚወስዱ አስታውቀዋል። በአሜሪካ እስካሁን ከ 9 ሺ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። 150 ያክል ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል።

በአሜሪካ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እንዳሉ ይገመታል።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: