ቤተሰቦች ከእስረኞች ጋር እንዳይገናኙ እገዳ ተጣለ

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ሲባል በፌደራል ደረጃ የሚገኙ እስረኞች ለሁለት ሳምንታት ያክል ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዳይገናኙ እገዳ ተጥሏል።

ፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር በአገሪቱ ከተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ታራሚዎችን ለመጠበቅ ሲባል ለመጪዎቹ 15 ቀናት ታራሚዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዳይገናኙ እግድ መጣሉን አስታውቋል።

እስረኞቹ ወደ ሆስፒታል የሚሄዱት የከፋ ችግር ከገጠማቸው ብቻ መሆኑ ያስታወቀው የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር፣ እስካሁን ድረስ በበሽታው የተያዘ እስረኛ ስለመኖሩ አልገለጸም።

በኢትዮጵያ እስር ቤቶች በከፍተኛ ደረጃ የተጨናነቁና ደረጃቸውን ያልጠበቁ ናቸው። ኮርኖ ቫይረስ ጉዳት ያደርስባቸዋል ተብለው ከተለዩ ተቋማት አንዱ እስር ቤት ነው። አንዳንድ አገሮች በሽታውን በማስመልከት ቀላል ወንጀል ያለባቸው ሰዎች በምህረት ወይም በረጅም ቀጠሮ በመልቀቅ፣ የእስረኞችን መጨናነቅ ለመቀነስ እየሞከሩ ነው።

በኢትዮጵያ ተመሳሳይ እርምጃ ይወሰድ አይወሰድ መስሪያ ቤቱ የገለጸው ነገር የለም።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: