( ERF) ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በውጭ አገር ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ ካስታወቀ በሁዋላ ታላልቅ የሚባሉት የአለም የመገናኛ ብዙሃን ዜናውን እያራገቡ ነው። ቢቢሲን ጨምሮ ዘ ሂል እና ሌሎችም የመገናኛ ብዙሃን እያራገቡት ነው። ጥቃቱ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚሰሩ ጋዜጠኞችም ላይ ያነጣጠረ ነው።
የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ ” ቫይረሱ ከየትኛውም ሀገር ወይም ዜግነት ጋር ያልተያያዘ መሆኑን በመግለጽ፣ህዝቡን የማስተማር ስራ እንደሚሰራ ግልጿል። ” ቫይረሱን የመከላከል ጥረታችን ሰብአዊነታችንን የሚጋርድ እና ርኅራሄን የሚያስጥል መሆን አይኖርበትም። የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አካል እንደ መሆናችን፣ አንዳችን የአንዳችን ጠባቂዎች ነን። የበሽታ ፍርሃት ሰብአዊነታችንን እንዲነጥቀን አንፍቀድ።” በማለትም አክሏል።
መንግስት እንዲህ አይነት ኢ ሰብዓዊ ድርጊት በሚፈጽሙ አጥፊዎች ጠንከር ያለ እርምጃ ካልወሰደ ድርጊቱ እየተባባሰ ሄዶ የውጭ አገር ዜጎችም ኢትዮጵያን ጥለው እንዳይወጡ ስጋት አሳድሯል።