“ወጣቶች እናንተም ልትሞቱ ትችላላሁ”

( ERF) የአለም የጤና ድርጅት መሪ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ለወጣቶች ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። "ወጣቶች የማትደፈሩ እንዳይመስላችሁ። ይህ ቫይረስ እናንተንም ለሳምንታት ሆስፒታል ውስጥ ሊያስተኛችሁ ይችላል። ሊገላችሁም ይችላል። ባትታመሙ እንኳን እናንተ የምትሄዱበት ቦታ የአንድን ሰው ህይወት በመኖርና በመሞት መካከል ሊያደርገው ይችላል"ሲሉ ተናግረዋል። በእድሜ የገፉ ሰዎች ዋነኞቹ የበሽታው ተጠቂዎች ቢሆኑም፣ በሽታው ወጣቶችንም አይምርም። በተለያዩ አገራት ያሉት መረጃዎች... Continue Reading →

ወደ 30 አገሮች የሚደረጉ በረራዎች ተቋረጡ

( ERF) ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር ሲባል ወደ 30 አገራት የሚደረጉ በረራዎች ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጥ ተወስኗል ብለዋል። እገዳ ካልተጣለባቸው አገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ዜጎችም ለ 2 ሳምንታት ራሳቸውን አግልለው እንዲቀመጡ ይደረጋል። አየር መንገዱ ወደ የትኞቹ አገራት በረራ እንዳቋረጠ በዝርዝር የቀረበ ነገር የለም። በርካታ አገሮች ወደ ኢትዮጵያ በረራ ያቆሙ በመሆኑ የኢትዮጵያ... Continue Reading →

እምነትን ፈተና ላይ የጣለው ኮሮና

የሰው ልጅ እምነት ወይም ሃይማኖት የሚፈተነው አደገኛ በሽታ ሲከሰት ነው። አንዳንዱ እኔ የማመልከው ፈጣሪ ያድነኛል ብሎ ሙሉ እምነቱን ወደ ፈጣሪው ያደርጋል። ሌላው ደግሞ  ሳይንስ የሚለውን መከተል ይመርጣል። እንደ ኮሮና ቫይረስ አይነት አደገኛ ወረርሽኝ ሲመጣ ሰዎች “ ወደ ክሊኒክ ልሂድ ወይስ ወደ ቤተ ክርስቲያን?” በሚል እምነትን በሚፈታተን ጥያቄ ይወጠራሉ። በአውሮፓ ብዙ ሰዎች ሃይማኖታቸውን እየተው ሳይንስን መከተል... Continue Reading →

ጎንደር ሌሊቱን በጥይት ድምጽ ስትረበሽ አደረች

( ERF) የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ፋኖ በሚል ስም በተለያዩ መንገዶች ተደራጅተው ዝርፊያ ይፈጽማሉ ባላቸው ታጣቂዎች ላይ የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ፣ ከተማዋ ሌሊቱን በተኩስ ስትናወጥ አድራለች ። የከባድ መሳሪያ ድምጾች የሰሙ እንደነበር የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ በተኩሱ ጉዳት የደረሰበት አካል ስለመኖሩ ግን እርግጠኞች መሆን አልቻሉም። ፋኖን በተመለከተ የከተማው ህዝብ በሁለት ተከፍሏል። በፋኖ ስም የሚዘርፉና የከተማውን ህዝብ ሰላም የሚነሱ በአንድ... Continue Reading →

Blog at WordPress.com.

Up ↑