ወደ 30 አገሮች የሚደረጉ በረራዎች ተቋረጡ

( ERF) ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር ሲባል ወደ 30 አገራት የሚደረጉ በረራዎች ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጥ ተወስኗል ብለዋል። እገዳ ካልተጣለባቸው አገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ዜጎችም ለ 2 ሳምንታት ራሳቸውን አግልለው እንዲቀመጡ ይደረጋል። አየር መንገዱ ወደ የትኞቹ አገራት በረራ እንዳቋረጠ በዝርዝር የቀረበ ነገር የለም። በርካታ አገሮች ወደ ኢትዮጵያ በረራ ያቆሙ በመሆኑ የኢትዮጵያ መንግስት የወሰደው እርምጃ የሚጠበቅ ነበር።

በሌላ በኩል  የሃማኖት ተቋማት የአምልኮ ስርዓታቸውን በተመለከተ መግለጫ እንደሚሰጡ ዶ/ር አብይ ተናግረዋል።

እስረኞችን ወደ ተለያዩ አካባቢዎች በማዛወር መጨናነቅን ለመቀነስ እንዲሁም የመፈቻ ጊዜያቸው የደረሰና ወንጀላቸው ቀላል የሆኑትን አይቶ ለመፍታት መታቀዱም ተነገሯል። የምሽት የጭፈራ ቤቶችም ይዘጋሉ። መንግስት ራሱ በየጊዜው የሚያደርገውን ስብሰባ ስለመግታቱ ግን  ጠ/ሚኒስትሩ ያሉት ነገር የለም።

በውጭ አገር ዜጎች ላይ የሚደረገው ጥቃት ኢትዮጵያዊ ባህል እንዳልሆነና በፍጥነት መቆም እንዳለበትም ጠ/ሚኒስትሩ አሳስበዋል። ድርጊቱ ለኢትዮጵያ ያልተገባ ስም እንዳያሰጥ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባልም ብለዋል። በሽታው በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያደርስበት የገለጹት ጠ/ሚኒስትሩ፣ ጉዳቱን ለመቀነስ የሚያስችሉ ጥናቶች እየተካሄዱ ነው።

የበጎ አገልግሎት የሚሰጡ ወጣቶች ዜጎችን ለመርዳት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ የተለዬ  ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው እንዲሁም የህክምና ባለሙያዎች እና በትምህርት ላይ የሚገኙት ሁሉ ዜጎችን ለመርዳት ዝግጁ እንዲሆኑ ጠ/ሚኒስትሩ ጠይቀዋል።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: