“ወጣቶች እናንተም ልትሞቱ ትችላላሁ”

( ERF) የአለም የጤና ድርጅት መሪ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ለወጣቶች ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። “ወጣቶች የማትደፈሩ እንዳይመስላችሁ። ይህ ቫይረስ እናንተንም ለሳምንታት ሆስፒታል ውስጥ ሊያስተኛችሁ ይችላል። ሊገላችሁም ይችላል። ባትታመሙ እንኳን እናንተ የምትሄዱበት ቦታ የአንድን ሰው ህይወት በመኖርና በመሞት መካከል ሊያደርገው ይችላል”ሲሉ ተናግረዋል።

በእድሜ የገፉ ሰዎች ዋነኞቹ የበሽታው ተጠቂዎች ቢሆኑም፣ በሽታው ወጣቶችንም አይምርም። በተለያዩ አገራት ያሉት መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ እድሜያቸው ከ 50 አመት በታች የሆኑ በብዛት የሆስፒታሎችን አልጋዎች አጣበው ይገኛሉ” ሲሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ አክለው ተናግረዋል።

ዶ/ር ቴዎድሮስ በቻይና ዛሬ በበሽታው የተያዘ አዲስ ሰው አለመኖሩ፣ አስከፊ የሆነውን በሽታ መቆጣጠር እንደሚቻል ተስፋ የሚሰጥ ነው ብለዋል።

የአለም የጤና ድርጅት እስካሁን 1 ሚሊዮን 500 ሺ የላብራቶሪ መመርመሪያ መሳሪያዎችን ወደ ተለያዩ አለማት ልኳል።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: