የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ታሪካዊ ውሳኔ አሳለፈች

(ERF) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሣዊ የስብከተ ወንጌል ጉባኤያትና የመንፈሳዊ ጉዞ መርሐ ግብሮች ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቆሙ ውሳኔ ማሳለፏን አቡነ ዮሴፍ ተናግረዋል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊና የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት የሆኑት አቡነ ዮሴፍ፣ በቅዳሴና በምሕላ ጸሎት ጊዜ በውስጥም ሆነ በአጸደ ቤተ ክርስቲያን ዘርዘር ብሎ በመቆም መንፈሳዊ አገልግሎቶችን እንዲፈጸሙ ቅዱስ ሲኖዶሱ መወሰኑን ተናግረዋል።

የግብጽ ኮፕቲክ ቤ/ክርስቲያን ማንኛውም አገልግሎት አቋርጣለች። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ እንደ ሌሎች አገሮች ቤ/ክርስቲያኖች አገልግሎቷን ሙሉ በሙሉ አላቋረጠችም ይሁን እንጅ በሽታው እየተሳፋፋ ከሄደ ቤተክርስቲያኑም አገልግሎቷን ልታቋርጥ የምትችልበት እድል ከፍተኛ ነው።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ሙስሊሙ ቤቱ ሆኖ መስገድ እንደሚችል ምክሩን ለግሷል

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤት ባወጣው መግለጫ ማንኛውም ሙስሊም በሽታው አስጊ በሆነበት በዚህ ሁኔታ ከጁምዓ እና ከጁምዓ መቅረት በሸርዓ የተፈቀደ በመሆኑ ህዝቡ በእየቤቱ መስገድ ይችላል ብሏል።

በኮሮና ቫይረስ በሽታ የተያዘ ወይም የተጠረጠር ማንኛውም ሰው ለጁምዓም ሆነ ለጁመዓ ሶላት፣ ለሃይማኖታዊ ትምህርት ወደ መስጅድም ሆነ ህዝብ ወደ ሚሰበሰብበት ቦታ መምጣት የተከለከለ ነው ሲል አሳስቧል።

የጤና ጥበቃ ተቋማት እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት የሚሰጡትን ምክርና መመሪያ መቀበል እና በስራ ላይ ማዋል ሃይማኖታዊ ግዴታ እንደሆነም ም/ቤቱ ገልጿል።

ምክር ቤቱ ወደ መስጊድ በመሄድ የሚደረገውን የጋራ የስግደት መረሃ ግብር ከመከልከል ተቆጥቧል።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: