በኢትዮጵያ በኮሮና የተያዘው ህዝብ ትክክለኛ አሃዝ በመንግስት ከተጠቀሰው በላይ ሊሆን እንደሚችል ጠ/ሚኒስትሩ ተናገሩ

(ERF) ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እውነተኛ ፍተሻ ቢካሄድ በበሽታው የተያዘው ቁጥር 11 ብቻ ላይሆን ይችላል ሲሉ፣ በመንግስት የሚገለጸው ቁጥር በሽታው በኢትዮጵያ የሚገኝበትን ደረጃ ትክክለኛ ማሳያ አለመሆኑ ገልጸዋል።

ጠ/ሚኒስትር አብይ “ከዚህ በላይ ፍተሻ ቢደረግ ቁጥሩ ሊያድግ ይችላል፣ መዘናጋት አያስፈልግም” ያሉ ሲሆን፣ ፍተሽው ውስንነት ያለበት መሆኑንም አምነዋል።

አንዳንድ ባለሙያዎች በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ  ሰዎች ቁጥር 11 ብቻ ተደርጎ የሚነገረውን አሃዝ ለመቀበል ይቸገራሉ። በአንዳንድ የአፍሪካ አገሮች በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር በመቶዎች እየተቆጠረ፣ የዲፕሎማሲ መናሃሪያ በሆነችው ኢትዮጵያ አነስተኛ አሃዝ መጠራቱ መንግስት መረጃውን ሆን ብሎ እየደበቀ ነው የሚል ጥርጣሬ አሳድሮ ነበር። ይሁን እንጅ ጠ/ሚኒስትሩ ችግሩ በቂ ምርመራ ካለማድረግ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ፍንጭ ሰጥተዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ በሃይማኖት ተቋማት ድርጊትም ማዘናቸውን ገልጸዋል። የሃይማኖት ተቋማቱ እየወሰዱት ያለው እርምጃ በቂ እንዳልሆነና ተጨማሪ እርምጃ እንዲወስዱ ግፊት እንደሚያደርጉ ዶ/ር አብይ ገልጸዋል።

ዶ/ር አብይ ስብሰባዎችን ለማስቆም አለመወሰኑን መናገራቸው ጥያቄ አስነስቶባቸዋል። ምርጫውን በማራዘም የፓርቲ ስብሰባዎችን መግታት አስፈላጊ መሆኑን የሚናገሩ ቁጥራቸው ቀላል አይደለም።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: