ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ለደህንነት ክፍሉ ትዕዛዝ ሰጡ

(ERF) ጠ/ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ እያሻቀበ የመጣውን የኮሮና ቫይረሰ ስርጭትን ለመግታት በሚል ለደህንነት መስሪያ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥተዋል። ትዕዛዙ ግን የተሟላ አይደለም ተብሏል።

ከዛሬ ከመጋቢት 14 ቀን ጀምሮ የደህንነት ዘርፉ በቁጥር የበዛ ሰው የሚሳተፍባቸውን ስብሰባዎች የሚያስቆም እና ማህበራዊ ርቀትን መጠበቀን ያስተገብራል። የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጨምሮ፣ የመንግስት ተቋማት ማህበራዊ ርቀትን ተፈጻሚ ማድረግ እና ስብሰባን ሲያካሂዱ ቫይረሱን ለመከላከል ቅድመ ጥንቃቄዎችን እንዲያደርጉም አዘዋል።

በመንግስት መስሪያ ቤቶች ተቀጥረው የሚሰሩት እንደ ሁኔታቸው ታይቶ ቤታቸው ተቀምጠው የሚሰሩበትን ሁኔታ እንዲያመቻች፣ የህዝብ ማመላለሻ አገልግሎት ሰጪዎች ሰዎችን አጨናንቀው መጫን እንደማይችል ፤ ብሄራዊ የመከላከያና የፖሊስ ሰራዊት ቫይረሱን ለመከላከል ዝግጅት እንዲያደርጉ ፤ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ተቋማት ላይ የሚወሰደ እርምጃ እንዲቀጥሉ እንዲሁም መከላከያ ሰራዊቱ በድንበር አካባቢ የሚደረጉ እንቅስቃሴውችን በሙሉ እንዲገታ መመሪያ ተላልፎለታል።

ውሳኔው ተገቢ ቢሆንም፣ ጠ/ሚኒስትሩ ስብሰባዎችን ለምን ማስቆም እንዳልፈለጉ ግልጽ አይደለም። አብዛኛዎቹ ስብሰባዎች እየተካሄዱ ያሉት በብልጽግና ፓርቲ ነው። ይህም የጠ/ሚኒስትሩን ትዕዛዝ ያልተሟላ ያደርገዋል የሚሉ አስተያየቶች ይቀርባሉ።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: