አሳዛኙ የኢትዮጵያውያን እልቂት በሞዛምቢክ

(ERF) ከ60 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከማላዊ ተነስተው ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲያቀኑ በአየር እጥረት ህይወታቸው አልፏል።  ክለብ ሞዛምቢክ ጋዜጣ እንደዘገበው 14 ኢትዮጵያውያን በህይወት ተርፈዋል። መኪናው ሞአቲዝ ወረዳ ዌይ ጣቢያ ላይ ሲደርስ፣ በህይወት የተረፉት ኢትዮጵያውያን ሲጮሁና መኪናውን ሲደበድቡ የሰሙት ፖሊሶች በጥርጣሬ መኪናውን አስቁመው ፍተሻ አድርገዋል። በፍተሻውም ከ 60 በላይ የሚሆን አስከሬን ሲያገኙ፣ በሞትና በህይወት መካከል ያሉ 14 ኢትዮጵያውያንን አትርፈዋል።

ፖሊሶቹ ወዲያውኑ ሾፌሩን በቁጥጥር ስር አድርገውታል። ሾፌሩ 25 ሰዎችን ብቻ እንዲጭን እንደተስማማ ተናግሯል። የሞዛምቢክ ፖሊስ አስከሬን የመለየት ስራ እየሰራ ሲሆን፣ በአገሪቱ ያለው አስከሬን የማቆያ ቦታ የሰው ሃይል እጥርት ያለበት በመሆኑ ስራው በተፋጠነ ሁኔታ እየተከናወነ አይደለም።

በህገወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚጓዙት ኢትዮጵያውያን አብዛኞቹ ከደቡብ የአገሪቱ ክፍል የሚመጡ ናቸው።

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኢትዮጵያውያን ሞት የተሰማውን ሃዘን ገልጾ፣ ደቡብ አፍሪካ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ እና በሞዛቢክ ከኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት ጋር እየተነጋገረ መሆኑን አስታውቋል። በድህነት ምክንያት አገራቸውን ጥለው ወደ ደቡብ አፍሪካ በህገወጥ መንገድ የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: