በዚህ አያያዙ ኦነግ ሸኔ ጠ/ሚኒስትሩንም ከመግደል አይመለስም

ኦነግ ሸኔ የመንግስት ባለስልጣናትን እየነጠለ የመግደልና ሽብር የመንዛት ስትራቴጂ ይከተላል። ይህን ስትራቴጂውን ቀደም ብሎ በነቀምቴ ባለስልጣናት፣ በቅርቡ በለገጣፎ ፖሊስ አዛዥ፣ ዛሬ ደግሞ በነቅምቴ የቀድሞ የአስተዳደርና ደህንነት ሃላፊ አቶ ተሾም ገነቲ ላይ ተግባራዊ አድርጎታል። ኦነግ ሸኔ እስካሁን በያቅጣጫው ከ 50 ያላነሱ የመንግስት ባለስልጣን አንድ በአንድ እያለቀመ አጥፍቷቸዋል። ይህንን ግድያ ለማስቀረት የኦሮምያ ክልል መንግስትና የፌደራሉ መንግስት ከፍተኛ... Continue Reading →

የኮሮና ቫይረስ መድሃኒት በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ሊሰጥ ነው

(ERF) በመላው አለም የሚገኙ ሳይንቲስቶች ከ 18 ሺ በላይ ሰዎችን የገደለውንና ከ410 ሺ በላይ ሰዎችን ደግሞ እያሰቃየ የሚገኘውን የኮሮና ቫይረስን ለማዳን ተቃርበዋል። የአለማቀፍ የጤና ድርጅት እንዳለው እስካሁን ከ 20 በላይ የክትባት ምርምሮች እየተካሄዱ ነው። ምርምሮች የተሳኩ ቢሆን እንኳን፣ ክትባቱን ለመጀመር ከ 1 አመት እስከ 1 አመት ከ 6 ወር ጊዜ ያስፈልጋል። ስለዚህ ሳይንቲስቶች ሌላ መድሃኒት... Continue Reading →

ለግብጽ ዛቻ ቁብ ያልሰጠው መንግስት ግድቡን ከ3 ወራት በሁዋላ ውሃ መሙላት ይጀምራል

(ERF) ግብጽ ኢትዮጵያ ያለ ስምምነት ውሃ መሙላት እንዳትጀምር ወታደራዊ ማስፈራሪያዎችንና የዲፕሎማሲ ዘመቻዎችን ስታካሂድ ቆይታለች። የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሹክሪን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣኖቿ የአረብና የአፍሪካ አገራት መሪዎችን በሮች ሲያንኳኩ ሰንብተዋል። በአረብ አገራት በኩል፣ ከሱዳን በስተቀር፣ "ከጎናችሁን ነን" የሚል ተሰፋ አግኝተዋል። ይሁን እንጅ የአረብ አገራቱ ትኩረት በኮሮና የተነሳ ተበታትኗል። በኢትዮጵያ በኩልም እንዲሁ በፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ፣... Continue Reading →

በፋኖና በመከላከያ ሰራዊት መካከል ያለው ፍጥጫ ቀጥሏል

የተሰጠው የጊዜ ገደብ በፍጥነት እየቀረበ ነው፤ አርበኛ መሳፍንት እጁን ለመስጠት ፈቃደኛ አይደለም (ERF) በፋኖና የአማራ ልዩ ሃይልን በካተተው የመከላከያ ሰራዊት መካከል ያለው ፍጥጫ እያየለ ሄዷል። የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ልዩነቱን በሽምግልና ለመፍታት ቢሞክሩም እስካሁን አልተሳካላቸውም። የጎንደር ከተማ የጸጥታው ምክር ቤት በፋኖ ስም ዝርፊያና ግድያ ይፈጽማሉ ያላቸው ታጣቂዎች፣ እስከ መጋቢት 20 ቀን 2012 ዓም ትጥቃቸውን እንዲፈቱ... Continue Reading →

Blog at WordPress.com.

Up ↑