የኮሮና ቫይረስ መድሃኒት በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ሊሰጥ ነው

(ERF) በመላው አለም የሚገኙ ሳይንቲስቶች ከ 18 ሺ በላይ ሰዎችን የገደለውንና ከ410 ሺ በላይ ሰዎችን ደግሞ እያሰቃየ የሚገኘውን የኮሮና ቫይረስን ለማዳን ተቃርበዋል። የአለማቀፍ የጤና ድርጅት እንዳለው እስካሁን ከ 20 በላይ የክትባት ምርምሮች እየተካሄዱ ነው። ምርምሮች የተሳኩ ቢሆን እንኳን፣ ክትባቱን ለመጀመር ከ 1 አመት እስከ 1 አመት ከ 6 ወር ጊዜ ያስፈልጋል። ስለዚህ ሳይንቲስቶች ሌላ መድሃኒት ግፋ ቢል በሚቀጥሉት 6 ሳምንታት ውስጥ ተግባራዊ ያደርጋሉ።


የእስራኤሉ ጀሩሳሌም ፖስት ታዋቂውን የተዋስያን ተመራማሪ ፕሮፌሰር ፒተር ጄይ ሆቴዝን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ በኮሮና ተይዘው የዳኑ ሰዎችን የደም መከላከያ (antibodies) በመውሰድና ለህመምተኞች በመስጠት የማከም ዘዴ (convalescent serum antibody therapy) በቅርቡ ይጀመራል። በአንዳንድ በጠናባቸው በሽተኞች ላይም ተግባራዊ ሆኗል

ይህን ዘዴ በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ወይም ወራት ውስጥ በስፋት ተግባራዊ የማድረግ ስራ እንደሚሰራ ከዚያም አዲስ የኬሚካል መድሃኒት በአንድ አመት ውስጥ፣ ክትባቱ ደግሞ ከ አንድ አመት እስከ 3 አመታት በሚደርስ ጊዜ ውስጥ እንደሚሰጥ ፕሮፌሰር ሆቴዝ ገልጸዋል።  

ከ18 ዓመታት በፊት የሳርስ ቫይረስ ይሰራጭ በነበረበት ወቅት ለኮሮና ቫይረስ ክትባት አግኝተው እንደነበር የገለጹት ፕሮፌሰሩ፣ በወቅቱ በገንዘብ እጥረትና በፍላጎት ማጣት የተነሳ ተግባራዊ ሳይደረግ ቀርቷል ብልዋል። አሁን ግን ያንን ክትባት እንደገና ለማስጀመር እየተሞከረ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በህብሪው ዩኒቨርስቲ የተዋስያን ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ሪቭካ አቡላፊያ ላፒድም እንዲሁ ቫይረሱን ለመከላከል የሚሰጠው መድሃኒት በሚቀጥሉት 6 ሳምንታት ካልሆነም ከዚያ በፊት ይቀርባል ብለዋል።

ዶ/ር ላፒድ ቀጣዩ ፈተና ይህን የተፈጥሮ መከላከያ በሺ ለሚቆጠሩ ሰዎች ማዳረስ ነው ይላሉ። ያም ሆኖ ግን አለም የመጀመሪያውን ውጤታማ መድሃኒት ለማየት ከ 6 ሳምንታት የበለጠ ጊዜ አይወስድበትም ሲሉ ዶ/ር አቡላፊያ ተስፋቸውን ገልጸዋል።
ኮሮና እንደ ኢንፍሎዊንዛ ራሱን የሚለዋውጥ በመሆኑ በእያመቱ አዳዲስ መድሃኒቶችን ማዘጋጀት አለብን ሲሉም ምክራቸውን አክለዋል።

Comments are closed.

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: