(ERF) የአለም የጤና ድርጅት መሪ ዶ/ር ቲዎድሮስ አድሃኖም በሰጡት መግለጫ ዛሬ በኖርዌይና ስፔን አራት አይነት መድሃኒቶች በተመረጡት በሽተኞች ላይ ሙከራ የደረግባቸዋል።
የመድሃኒት ሙከራውን ኮረናን ለመከላከል የተወሰደ ታሪካዊ እርምጃ መሆኑን በደስታ እገልጽላችሁዋለሁ ያሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ፣ ሌሎች 45 አገራትም በተመሳሳይ መንገድ ሙከራ ለማካሄድ ፈቃደኝነታቸውን ገለጸውልናል ብለዋል። ሌሎችም አገሮች በፍጥነት ሙከራውን ካካሄዱ፣ የመድሃኒቱን ውጤታማነት ቶሎ እናውቃለን ሲሉ አክለዋል።
ዶ/ር ቴዎድሮስ ክትባት ለመስራት ከአንድ አመት እስከ 1 አመት ከስድስት ወር እንደሚወስድ ተናገርዋል።
ይህ እስከሚሆን ድረስ ሌሎች ግልሰቦችና አገሮች በአለም የጤና ድርጅት እውቅና ያልተሰጣቸውን መድሃኒቶች ከመጠቀም እንዲቆጠቡም ጠይቀዋል።
መድሃኒቶችን ያለ ጤና ድርጅቱ እውቅና ለበሽተኞች መስጠት ችግሮችን ሊያስከትሉ ይችላሉ ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ዶ/ር ቴዎድሮስ በወረቀት ላይ ወይም በሙከራ ብልቃጥ ውስጥ ይሰራል የተባለ መድሃኒት ወደ ሰው ሲገባ ውጤት ላያመጣ ይችላል በማለት ኢቦላን በምሳሌነት አንስተዋል። ለኢቦላ መድሃኒት ተገኝቷል ከተባለ በሁዋላ ለሰዎች ሲሰጥ እንድተባለው ውጤታ አልሆነም ብለዋል።
የአለም የጤና ድርጅት ብዙ አገሮች በምርምሩ እንዲገፉበት ድጋፍ እየሰጠ መሆኑንና መስፈርቶችን በድረጉጹ ላይ ማስፈሩን ተናግረዋል።
ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሃኪሞች መሰልጠናቸውን እና የገንዘብ ድጋፍም እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል።
የኖርዌይ የጤና ሚኒስትር በበኩላቸው የዛሬውን ሙከራ ታሪካዊና ተስፋ የሚሰጥ ነው ብለዋል።
Leave a Reply