የኮሮና ቫይረስ መድሃኒት ሙከራ

( ERF) የአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ት ቴዎድሮስ አድሃኖም ታሪካዊ ያሏቸውን መድሃኒቶች ለመሞከር በኖርዌይና ስፔን ፈቃደኛ የሆኑ በበሽታው የተያዙ ሰዎችን መመዝገብ መጀመራቸውን አርብ እኤአ 28/03/2019 አሳውቀዋል። ለሙከራ የቀረቡት መድሃኒቶች የትኞቹ ናቸው? ነባሮቹ ወይስ አዲሶቹ? ውጤታቸውስ እንደታሰበው ይሳካ ይሆን?

ክትባት

የአለም የጤና ድርጅት (WHO) በቻይና ውሃን ከተማ ሳንባን የሚያጠቃ ያልታወቀ በሽታ መከሰቱን እኤአ በ31 December 2019 ከሰማበት ጊዜ አንስቶ የተለያዩ ታዋቂ የአለም ሳይንቲስቶችን በመሰብሰብ ስለበሽታው ባህሪ ለማወቅ ጥረት አድርጓል። የጤና ድርጅቱ የምርምርና ልማት ( research and development) ክፍል ለበሽታው የሚሆን ክትባትና መድሃኒት በፍጥነት እንዲፈለግ ባስታወቀው መሰረት፣ 2 ክትባቶች (vaccines) ለክሊኒካል ግምገማ ሲቀርቡ፣ 52 ክትባቶች ደግሞ ለቅድመ ክሊኒካል ግምገማ ቀርበዋል። ለክሊኒካል ግምገማ የቀረበው የመጀመሪያው ክትባት Adenovirus type 5 የሚባል ሲሆን፣ የሰሩትም CanSino Biological Inc. and Beijing Institute of Biotechnology የተባሉ ኩባንያዎች በጥምረት ነው። ሁለተኛው ክትባት ደግሞ LNP encapsulated mRNA የሚባል ሲሆን የሰራው ደግሞ Moderna/NIAID የተባለ ኩባንያ ነው። ዶ/ር ቴዎድሮስ እንደሚሉት ሁለቱን ክትባቶች ጥቅም ላይ ለማዋል ከ 1 አመት እስከ 1 አመት ከስድስት ወር ጊዜ ይወስዳል።

መድሃኒት

ክትባቱ ጥቅም ላይ እስከሚውል የሰዎችን ህይወት ለመታደግ ሊረዱ ይችላሉ የተባሉ አራት አይነት መድሃኒቶች በኖርዌና ስፔን በበሽታው በተያዙት ላይ ለመሞከር ምዝገባ ተጀምሯል። እነዚህ መድሃኒቶች የወባ በሽታንና የኤች አይ ቪ ቫይረስን ለማከም ጥቅም ላይ ሲውሉ የነበሩ ናቸው። አንደኛው ኢትዮጵያኖች በብዛት የሚያውቁትና በፈዋሽነቱ የሚተማመኑበት የወባ መድሃኒቱ ክሎሮኩዊን chloroquine እና ሃይድሮሲክሎሮኩዊን hydroxychloroquine ነው። ሌሎች መድሃኒቶች ደግሞ ለኤች አይ ቪ መድሃኒት ጥቅም ላይ የሚውሉት Lopinavir and Ritonavir እና interferon-beta ናቸው። እነዚህ መድሃኒቶች እንደአስፈላጊነቱ በተናጠል ወይም እየተቀላቀሉ ለበሽተኞች ይሰጣሉ።

የወባ መድሃኒት የሆነውን ክሎሮኩዊንን በተመለከተ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጥቅም ላይ እንዲውል ሃሳብ ሰንዝረው ነበር። የአለም የጤና ድርጅትም በክሎሮኩዊን ላይ የሚመክር ውይይት በጥር ወር መጨረሻ  ላይ ከታዋቂ ሳይንቲስቶች ጋር አካሂዶ ነበር። በስብሰባው እለት በክሎሮኩዊን ላይ 500 የክሊኒክ ሙከራዎች ቻይና ውስጥ መደረጋቸውንና 13 ሙከራዎች ውጤታማ መሆናቸውን የጤና ድርጅቱ አስታውቋል። ይሁን እንጅ በመድሃኒቱ ላይ ተጨማሪ ምርመራ እንደሚያስፈልግ በመስማማት ስብሰባውን አጠቃሏል።

የፈረንሳይ ታዋቂ ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ዲድየር ራውልት ክሎሮኩዊን ኮሮና ቫይረስን እንደሚፈውስ ማረጋገጣቸውን አስታውቀዋል። ፕሮፌሰሩ ክሎሮኩዊን መድሃኒት የተሰጣቸው በሽተኞች በፍጥነት ማገገማቸውንና በሽታው እንዳይዛመት ማድረጉን ገልጸዋል።

የእነዚህ መድሃኒቶች ውጤት የሚታወቀው በርካታ አገሮች ሙከራው እንደተሰካ ከገለጹ በሁዋላ ነው። እስካሁን 45 አገራት መድሃኒቶቹን ለመሞከር ተስማምተዋል። ብዙ አገራትም ፍላጎታቸውን እየገለጹ ነው። መድሃኒቶቹን ለመሞከር የሚወስደው ጊዜ አጭር ነው። መረጃዎቹን ሁሉ አሰባስቦ ለመላክ እና በዚያ ላይ ተመስርቶ ውሳኔ ለመወሰን ግን የተወሰነ ጊዜ ይወስዳል።

ታሪካዊ የተባለው ሙከራ ከተሳካ ከ 20 ሺ በላይ ሰዎችን ለገደለውና ወደ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ሊያጠቃ ይችላል ተብሎ የሚገመተውን የ ኮሮና ቫይረስ በሽታን ጉልበት ማዳከም ይቻላል። እስከዚያ ድረስ የአለም የጤና ድርጅትና የጤና ባለሙያዎች የሚሰጡትን ምክር ተግባር ላይ ማዋል የግድ ይላል።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: