ጥርጣሬዎችን ሁሉ በስራ የሚያፈርስ ከንቲባ

ታከለ ኡማ የአዲስ አበባ ከንቲባ ሆኖ ሲሾም ብዙ ጫጫታዎች ነበሩ። “የኦነግ አጀንዳ ተሸካሚ ነው፤ አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት የሚል አመለካከት አለው፤ የአዲስ አበባን መስተዳድር ስልጣን በኦሮሞዎች ብቻ አስያዘው፤ መሬት ለኦሮሞዎች እየሸነሸነ ሰጠ፤ ቄሮን አደራጅቶ በባልደራስ ላይ ጥቃት እንዲፈጸም አስደረገ” የሚሉና ሌሎችም ወንጀሎች ይቀርቡበት ነበር። “ታከለ ኡማ የኦነግ ጎማ” እየተባለ በየስብሰባው ተወግዟል። ታከለ ስልጣን ይልቀቅ የሚሉ ጥያቄዎችም ከብአዴን የአዲስ አበባ አባላት ሳይቀር ቀርቦበታል። “ታከለ ለፎቶ ሲል የሚሰራ ነው” በማለት የብአዴን አባላቱ ወንጅለውታል። አንድ ሰሞን ከስልጣን ለቀቀ ተብሎ በተቃዋሚዎቹ ዘንድ ጉሮወሸባዬ ተጨፍሯል። በአቶ ለማ የተነሳ ከዶ/ር አብይ አህመድ ጋር አለመግባባት እንደፈጠረና ዶ/ር አብይ እንዳባረረውም ተወርቷል ። ወጣቱ ከንቲባ ታከል ግን እነዚህን ሁሉ ሟርቶች በስራ እያሸነፈ፣ በተለይ ሰሞኑን ደግሞ የችግር ጊዜ መሪ መሆኑን ኮሮና ለመከላከል በሚያደርገው ጥረት አሳይቷል።

ታከለ የአዲስ አበባ ደሃ ተማሪዎች በነጻ ምግብ እንዲመገቡ የሚያደርግ ውሳኔ ሲያሳልፍ ብዙዎቹ “አይሳካለትም” እያሉ አሹፈውበት ነበር። ግን ተሳካለት። ብዙ ደሃ ተማሪዎች እየተራቡ እንዳይማሩ በማድረግ ታሪካዊ ስራ ሰራ። ለተማሪዎች ደብተር በነጻ ከማከፋፈልና ለጎዳና ተዳዳሪዎች መጠለያ ከመስጠት ጀምሮ ብዙ የሚያስጨበጭቡ ስራዎችን ሰርቷል።

የኮንዶሚኒየም ቤቶችን ለቄሮ ሊሰጥ ነው ተብሎ አሉባልታ ሲናፈስበት፣ ቤቶቹን ለባለቤቶቹ ለማስረከብ ሲነሳ፣ ጀዋር ቄሮን ሰብስቦ ለማስቆም ሞከረ። የኦሮምያ መስተዳደር ጣልቃ በመግባቱ ሁለቱ መስተዳድሮች እየተወዛገቡ ይገኛሉ ። በአዲስ አበባ መስተዳደር ስር ያሉትን ኮንዶሚኒየሞች ለባለእደለኞች አከፋፈለ።

ታከለ ጸረ ኦርቶዶክስ ተደርጎ ሲወገዝ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ ግን ለኦሮቶዶክስ ቤ/ክ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ አሰርቶ የሰጠው እሱ ነው። ጸረ እስላም ተደርጎ ሲተችም ነበር። ለሙስሊሞች የሚገባቸውን የይዞታ ማረጋገጫ ለመስጠት እየሰራ መሆኑ ሲታወቅ ተችዎች አፋቸውን ያዙ። ታከለ በቅንጦት ይኖራል እየተባለ በፌስቡክ ሲብጠለጠል፣ መኖሪያ ቤቱን ለአቡነ መርቆሪዮስ መኖሪያ ይሆናቸው ዘንድ አሳለፎ ሰጠ።

ታከለ ቤት ለሌላቸው ድሃ እናቶች ቤት ሰርቶ ያስረከበ የድሆች እረዳት መሆኑን አሳይቷል።

ታከለ ኮሮናን ለመከላከል ሳምንቱን ሙሉ ሌት ተቀን እየሰራ ነው በዚህም እውነተኛ ከንቲባ፣ ተስፋ የሚጣልበት ሰርቶ የሚያሰራ የአገር መሪ መሆኑን አሳይቷል። በውጭ አገር እንደምናያቸው ከንቲባዎች፣ ከህዝብ ጋር እየተቀላቀለ ለምመከር፣ ለማበረታታት ጥረት ያደርጋል። መደገፍ ያለባቸው ድሆች እንዲደገፉ፣ መመከር ያለባቸው ወጣቶች እንዲመከሩ ይታትራል። የአለም መዲና የሆነችውን አዲስ አበባ የኮሮና በሽታ ምን ያክል ሊገድላት እንደሚችል ታደለ በደንብ ገብቶታል። ይህ እንዳይሆን ከእሱ የሚጠበቅበትን ሁሉ እየተወጣ ነው።

ፖለቲካው ሁሉ በብሄር ስለተቃኘ የኦሮሞ ብሄርተኞችም ሆኑ የአማራ ብሄርተኞች የሚሰራውን ስራ ሲያጣጥሉ እናያለን። ማንም ምን ይበል ታከለ ለ ከተማችን የሚገባት ከንቲባ ነው። ይህ ግን ጅማሮ ነው። ከታከለ ብዙ እንጠብቃለን። የከተማ መስተዳድሩን ቢሮክራሲ እንዲያስተካከል፣ የመሰረተ ልማት ችግሮችን እንዲቀርፍ ፣ አዲስ አበባን እንደ ስሟ አበባ እናደርጋታለን ያለውን በልማት ብቻ ሳይሆን በአስተሳሰብም እንዲቀርጻት እንፈልጋለን። በህወሃት ዘመን መሬት የሰበሰበውና ጥልፍልፍ ኔትወርክ የመሰረተው በታከለ ኡማ ላይ ብዙ እንደሚያስወራ ይታወቃል። አንተ ግን እውነትን ብቻ ይዘህ ቀጥል። ቢሮክራሲውን ከማጽዳትም ወደኋላ አትበል።

ታከለ ጥርጣሬዎችንና ውግዘቶችን በስራ እያፈረሰ መሪነቱ እያስመሰከረ በመሄድ ላይ ነውና በርታ እንበለው።

አሳምነው ጸበሉ

ጉርድ ሾላ   

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: