“ብ/ጄ አሳምነው ጽጌ ፌስቡክ ያገነነው ጦር መርቶ የማያውቅ ሰው ነው ሲሉ” ጓደኛው ተናገሩ


(ERF) የብ/ጄ አሳምነው ጽጌ የቅርብ ጉዳኛ የነበሩትና ከዚህ ቀደም በመፈንቅለ መንግስት ተጠርጥረው 2 ጊዜ ለእስር የተዳረጉት ጄ/ል ተፈራ ማሞ፣ አሳምነው የኢህአዴግን ሰራዊት ዘግይቶ የተቀላቀለ ጦር መርቶ የማያውቅ ሰው ነበር ሲሉ ለአንድ የአማራ ሚዲያ ተናግረዋል።


“አሳምነው ጦር አልመራም ስራው ሰዎችን ማደራጀት ነበር” ሲሉ ጄ/ል አሳምነው በቂ ወታደራዊ ልምድ እንዳልነበረውም ተናግረዋል።


አሳምነው አቅዶ መስራት የማይችል፣ በክልሉ ለተፈጠረው የሰላም መደፍረስ የእሱ የአመራር ብልሽት አስተዋጽኦ ማድረጉንና ራሱን ለማንገስ የፌስቡክ ደጋፊዎችን ቀጥሮ ስለራሱ ብዙ ያስነግር እንደነበር ጄ/ል ተፈራ አጋልጠዋል።
ስራውን አቅዶ እንዲሰራ በተደጋጋሚ ቢነገረውም ሊፈጽም አለመቻሉን የተናገሩት ብ/ጄ ተፈራ ማሞ፣ ግድያውን ከመፈጸሙ ከአራት ቀናት በፊት በም/ል ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን ሰብሳቢነት የክልሉ የጸጥታ አመራሮች ባሉበት ተግምግሞ እንደነበርም ተናግረዋል።


አሳምነው በሚዲያ ሊነገሩ የማይችሉ ብዙ ጥፋቶችን የሰራ ሰው እንደሆነ የገለጹት ብ/ጄ ተፈራ፣ አካሄዱን እንዲያስተካክል በተደጋጋሚ ቢመክሩትም ሊሰማ አለመቻሉን ተናግረዋል።


ሟቾቹ እነ አቶ ምግባሩና ዶ/ር አምባቸው አሳምነው ሊገድላቸው እንደሚያስብና መቺ ሃይልም እያሰለጠነ መሆኑን ነግረውት ነበር ሲሉም ጄ/ል ተፈራ አስረድተዋል።


ጄ/ል ተፈራ የሰጡት መረጃ የአሳምነው ጽጌን ደጋፊዎች ብዥታ ውስጥ የሚከት ነው። ጄ/ል ተፈራ በአማራ ህዝብ ዘንድ ያላቸው ከበሬታና አሳምነውን በቅርብ የሚያውቁት መሆናቸው እንዲሁም ከሰኔ 15ቱ ድርጊት ጋር በተያያዘ ታስረው የተፈቱ መሆናቸው የሚሰጡዋቸውን መረጃዎች ተአማኒት ከፍ ያደርገዋል። ጄኔራሉ በአማራ ክልል ባለስልጣኖች ዘንድ የሚያዩዋቸውንም ችግሮች ሳይደብቁ በድፍረት ተናግረዋል።


ጠ/ሚ አብይ አህመድ ጄ/ል አሳምነውን አስገድለውታል በሚል ሲወገዙ ቆይተዋል። ጠ/ሚንስትሩ በቅርቡ ዱባይ ላይ ተገኝተው በነበረበት ወቅት ለአሳምነው ብዙ ውለታ እንደዋሉለትና እውነቱ አንድ ቀን እንደሚጋለጥ ተናግረው ነበር። የብ/ጄ ተፈራ ማሞ ንግግር ዶ/ር አብይን ነጻ የሚያወጣቸውና በክልሉ ህዝብ ዘንድ የነበራቸውን ተቀባይነት መልሰው ለማግኘት እንደሚረዳቸው ይታመናል።

አስራት ቴሌቪዥን ከብ/ጄ ተፈራ ማሞ ጋር ተመሳሳይ ቃለ ምልልስ አድርጎ የነበረ ቢሆንም፣ ቃለምልልሱን ለማውጣት እንዳልፈለገ በተቋሙ ውስጥ የሚሰራው ጋዜጠኛ አያሌው መንበር አጋልጧል። አስራት ቴሌቪዥን መረጃውን ለምን አፍኖ ማስቀረት እንደፈለገ እስካሁን የሰጠው ማብራሪያ የለም።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: