ከኮሮና ጋር ተያይዞ የጥላቻ ንግግሮች ቀንሰዋል

(ERF) የኮሮና በሽታን ተከትሎ በኢትዮጵያ ይታዩ የነበሩ የጥላቻ ንግግሮች መቀነሳቸውን መረጃዎች አመለከቱ።

የጥናት ክፍላችን ባደረገው የዳሰሳ ቅኝት ከብሄርና ከፖለቲካ ጋር ተያይዞ ይቀርቡ የነበሩ የጥላቻ ንግግሮች በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሰዋል።

የብሄር ፖለቲካን ዋና አጀንዳቸው አድርገው የተለያዩ የጥላች ንግግሮችንና ልዩነቶችን ሲጽፉ የነበሩ የማህበራዊ አክቲቪስቶች አብዛኛው ጽሁፋቸው በኮሮና በሽታ ላይ ማተኮሩን ቅኝቱ ያሳያል። በአማካኝ በፌስቡክ ይቀርቡ የነበሩ አንዱን ወይም ሌላውን ብሄር በጥላቻ የሚያዩ ወይም የሚፈርጁ ጽሁፎች ከ70 በመቶ በላይ ቀንሰዋል።

መንግስትን ከብሄር ፖለቲካ ጋር አያይዘው ይተቹ የነበሩ ጽሁፎችም እንዲሁ ከ75 በመቶ በላይ ቀንሰዋል። በመንግስት ላይ የሚቀርቡት አብዛኞቹ ትችቶች መንግስት በሽታውን ለመከላከል ከሚወስዳቸው እርምጃዎችና ከሚሰጣቸው መረጃዎች ጋር የተያያዙ ናቸው።

በጎንደር አካባቢ በሚንቀሳቀሱ ፋኖዎች ላይ መንግስት ሊወስደው አቅዷል ከተባለው እርምጃ ጋር በተያያዘ፣ የአማራ ብሄርተኞች በክልሉና በፌደራል መንግስቱ ላይ ዘመቻ የከፈቱ ቢሆንም፣ ባለፉት ሁለት ቀናት ትኩረታቸው ወደ ኮሮና ዞሯል። በአማራ ክልል የሚታየው የኮሮና ስርጭት ስጋት ላይ የጣላቸው አክቲቪስቶች፣ የክልሉ መንግስት ተጨማሪ እርምጃዎችን እንዲወስድ የሚገፋፉ ጽሁፎችን እያወጡ ነው።

ከሃይማኖት ጋር ተያይዞ ይሰራጩ የነበሩ የጥላቻ ንግግሮችም በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሰዋል። ከ80 በመቶ በላይ የሚሆኑ ጽሁፎችና ስብከቶች ፈጣሪ ምህረቱን እንዲያወርድ የሚጠይቁ ናቸው።

የዳሰሳ ቅኝቱ እንደሚያሳየው ምንም እንኳን አብዛኛው ህዝብ የሃይማኖት ተቋማት ለበሽታው መስፋፋት አስተዋጾ እንደሚያደርጉ ቢገነዘቡም፣ የቤተክርስቲያንና የመስጊድ ደጆች እንዲዘጉና ምዕመናን በቤታቸው ሆነው እንዲያመልኩ ፍላጎቱ የላቸውም።

አብዛኛው ህዝብ የኮሮና በሽታ በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሞት ጉዳት ያደርሳል ብሎ ይሰጋል። ለዚህም የሚቀርበው ምክንያት ህዝቡ በበቂ ሁኔታ ራስን የመከላከል እርምጃ እየወሰደ አይደለም የሚል ቢሆንም፣ በርካታ ኢትዮጵያውያን የተለያዩ በሽታዎች ተጠቂ መሆናቸው፣ የህክምና ስርዓቱ ደካማ መሆንና የህዝቡ የኑሮ ሁኔታ ለጉዳቱ ተጨማሪ ምክንያቶች እንደሚሆኑ ይጠቅሳሉ።

ብዙ ኢትዮጵያውያን የኮሮና መድሃኒት በባህላዊ ህክምና መከላከል እንደሚቻል ያምናሉ። ይሁን እንጅ መደሃኒቱ በፍጥነት ከጤና ተቋማት ጋር በተቀናጀ ሁኔታ እንዲሰጥ ፍላጎታቸውን መሆኑንም የዳሰሳ ቅኝቱ ያሳያል።

ከ60 በመቶ በላይ የሚሆኑ ዜጎች መንግስት በሽታውን ለመከላከል በቂ ስራ እየሰራ ነው ብለው ያምናሉ። ይሁን እንጅ መንግስት ስራውን ዘግይቶ እንደጀመረና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለበሽታው መስፋፋት ዋና ተጠያቂ እንደሆነም ይናገራሉ።

በኢትዮጵያ ካሉ ባለስልጣናት ኮሮናን በተመለከተ ማን የተሻለ ስራ እየሰራ እንደሆነ የተጠየቁት አንዳንድ መላሾች፣ ዶ/ር አብይ አህመድ፣ አቶ ታከለ ኡማ፣ ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ አቶ ደመቀ መኮንንና ዶ/ር ደብረጺዮንን መርጠዋል።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: