እውን ኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር ደብቃለች?

(ERF) በርካታ ኢትዮጵያውያን የኮሮና ቫይረስ ተሸካሚ ህሙማን ቁጥር እንዴት አነስተኛ ሆነ እያሉ በመጠየቅ ላይ ናቸው። ጥያቄውን የሚያቀርቡት ደግሞ ከህክምና ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ አንዳንድ ሃኪሞችም ይገኙበታል። ታዲያ ጥያቄው ተገቢ በመሆኑ በጉዳዩ ዙሪያ የተለያዩ ሃኪሞችን አነጋግረናል።

እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ የአለም የስብሰባ ማዕከልና የቱሪዝም መዳረሻ ከሆኑ ጥቂት አገራት መካከል አንዷ ናት። በዚህም በርካታ የውጭ ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ይጎርፋሉ። ከንግድ እና ከኢንቨስትመንት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ቻይናውያን፣ ደቡብ ኮሪያውያን፣ ጃፓኖችና አውሮፓውያን በብዛት ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሽታው ወደ ተስፋፋባቸው የምስራቅ እስያ አገራት በረራ ያቋረጠው በቅርብ ነው። ወደ አንዳንድ አውሮፓ አገራት የሚያደርገውን በረራ ዛሬም ድረስ አላቋረጠም። በአጠቃላይ ሲታይ በአፍሪካ ውስጥ በቀላሉ ለበሽታው ተጋላጭ ከሆኑ ሁለት ወይም ሶስት አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ናት። ሌሎቹ እንደ ደቡብ አፍሪካ፣ ግብጽና ናይጀሪያን የመሳሰሉ መናሃሪያ አገራት በኮሮና የተያዙ ዜጎቻቸው በ ሺዎችና በመቶዎች እንደሚቆጠሩ ሲያስታውቁ ፣በኢትዮጵያ ግን ባለፉት 2 ሳምንታት በቫይረሱ የተያዘው የሰው ቁጥር ከ 30 አለዘለለም። ለዚህም ነው አንዳንዶች “መንግስት ቁጥሩን እየደበቀነ ነውን?’ የሚል ጥያቄ ማንሳት የጀመሩት።

ኢ አር ኤፍ ያነጋገራቸው ዶክተሮች የኢትዮጵያ መንግስት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር ሆን ብሎ እየቀነሰ ያስታውቃል ብለው አያምኑም። ቁጥሩን አሳንሶ መናገር ጉዳት እንጅ ጥቅም እንደሌለው መንግስት ይገነዘባል ብለው ያስባሉ። በእርግጥ ቀደም ብሎ በሳንባ ምች ( ኒሞኒያ) የሞቱ ሰዎችን መመርመር ስላልተቻለ፣ ሰዎቹ በኮቪድ 19 ይሙቱ አይሙቱ አይታወቅም። ይሁን እንጅ በኮቪድ 19 ላይ ምርምራና ክትትል መደረግ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የሚሰጡ መረጃዎች ትክክል ናቸው የሚል እምነት እንዳላቸው ሃኪሞች ይናገራሉ። ነገር ግን በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር አነስተኛ የሚመስለው በቂ ምርመራ ስለማይካሄድ ነው የሚል አስተያየት አላቸው። የአገሪቱ ህዝብ ቁጥር ከ100 ሚሊዮን በላይ ነው። እስካሁን የተመረመሩ ሰዎች ቁጥር ግን ከ 1 ሺ 100 አይበልጥም፣ ይህም በመሆኑ ቁጥሩ አነስተኛ መስሎ ታይቷል ሲሉ ምክንያታቸውን ያስቀምጣሉ። ኢትዮጵያ በርካታ ዜጎችን ለመመርመር የሚያስችል አቅም የላትም የሚሉት ባለሙያዎች፣ በአንድ ጊዜ በ10 እና በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን መመርመር ቢቻል አስደንጋጭ ቁጥር ሊመጣ ይችል ነበር ይላሉ።

የአለም የጤና ድርጅት ምርመራ አድርጉ የሚለው በቂ የመመርመሪያ መሳሪያ በሌለበት ሁኔታ ነው ሲሉም ያለውን ችግር ያስረዳሉ

በኢትዮጵያ ውስጥ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል የተፋጠነ ምርመራ ማድረግና የጤና ባለሙያዎች የሚሰጡዋቸውን ምክሮች ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ሃኪሞች ያሳስባሉ። በየአካባቢው ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች በፍጥነት ስለበሽታው የግንዛቤ ትምህርት መስጠት አስፈላጊ መሆኑንም ያሰምሩበታል።

የኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር መንግስት ባለው አቅም ዝግጅት ማድረጉን በተደጋጋሚ ሲገልጹ ቆይተዋል።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: